ሕዳር 19 ቀን 2019(መናኸሪያ ሬዲዮ) በምስራቅ ቻይና የምትገኘውና በኢኮኖሚዋ በከፍተኛ ፍጥነት በማደግ ላይ ያለችው የጂያንግሱ ግዛት፣ በአሁኑ ወቅት በአስደናቂውና ዘመናዊው የቤት አሰራር ስልቷ ምክንያት የማህበራዊ ሚዲያ ዋነኛ መነጋገሪያ ሆናለች።
ብዙዎች በማህበራዊ ሚዲያ ላይ የሚዘዋወሩትን የእነዚህን መንደሮች ምስሎችና ቪዲዮዎች ሲመለከቱ በኮምፒውተር ግራፊክስ የተሰሩ አስመስለው ቢጠራጠሩም፣ ምስሎቹ ግን በገሃድ መሬት ላይ ያሉ እውነተኛ የልማት ውጤቶች መሆናቸው ተረጋግጧል።
ይህ አይነቱ እይታ የቻይና መንግስት የገጠር አካባቢዎችን ለማዘመንና የከተማና የገጠርን የኑሮ ልዩነት ለማጥበብ የቀረጸው ሰፊ ስትራቴጂ አካል ሲሆን፣ በነዚህ መንደሮች ውስጥ ያሉ የገበሬዎች መኖሪያ ቤቶች በዘፈቀደ ሳይሆን በመንግስት መሃንዲሶች በጥናት ተቀርጸው ወጥ በሆነ ዲዛይንና መሠረተ ልማት የተገነቡ ናቸው።
ከመኖሪያ ቤቶቹ ጎን ለጎን የሚታዩት ሰፋፊ አረንጓዴ እርሻዎችም ቢሆኑ በዘመናዊና ወጥ በሆነ የካሬ መስመር የተከፋፈሉ በመሆናቸው፣ አካባቢው ከላይ ሲታይ ለዓይን እጅግ ማራኪና ልዩ ገጽታን አላብሶታል።
ይህ አስደናቂ ስኬት ቻይና የግብርናው ክፍለ ኢኮኖሚ ከዘመናዊው የመኖሪያ አካባቢ ጋር በማዋሃድ ረገድ የደረሰችበትን ከፍተኛ የቴክኖሎጂና የዲዛይን ደረጃ የሚያሳይ ሲሆን፣ ማህበራዊ ሚዲያ ላይ ለተመለከቱት በሚሊዮን የሚቆጠሩ የዓለም ህዝቦችም ትልቅ መነጋገሪያና ለሌሎች ሀገራት በትልቅ አርአያነት ሊጠቀስ የሚችል የልማት ተሞክሮ ሆኗል።
__
ሀሳብ እና’ሳ’ፍራለን
ምላሽ ይስጡ