ሕዳር 11 ቀን 2019(መናኸሪያ ሬዲዮ)በሳዑዲ ዓረቢያ ዋና ከተማ ሪያድ በሚገኘው የንጉሥ አብዱላህ የፋይናንስ ዲስትሪክት ውስጥ የሚገኘው የሀገሪቱ የሕዝብ ኢንቨስትመንት ፈንድ (PIF) ዋና መሥሪያ ቤት ሕንፃ ትናንት ኅዳር 10 ቀን 2019 ዓ.ም በደረሰ የሚሳኤል ጥቃት ጉዳት እንደደረሰበት ተገለጸ።
በየመን የሁቲ ታጣቂዎች ወደ ሪያድ የተተኮሰውን ሚሳኤል ለመመከት በተወሰደ እርምጃ ሳቢያ በወደቀ ፍርስራሽ በሕንፃው የተወሰኑ ፎቆች እና በአቅራቢያው በሚገኙ ሕንፃዎች ላይ ቁሳዊ ጉዳት መድረሱን የሳዑዲ ሲቪል መከላከያና የሀገሪቱ የዜና ወኪል (SPA) አረጋግጠዋል። ሆኖም በጥቃቱ ምክንያት በሰው ሕይወት ላይ የደረሰ ጉዳት አለመኖሩ ታውቋል።
ክስተቱን ተከትሎ የፋይናንስ ዲስትሪክቱ መግቢያዎች በሙሉ ተዘግተው ሰዎች ከአካባቢው እንዲወጡ ሲደረግ፣ አምቡላንሶችና የእሳት አደጋ መከላከያ ተሽከርካሪዎች በስፍራው መሰማራታቸውን ሮይተርስ ዘግቧል። በሪያድ ረጅሙን ሕንፃ የሚያቅፈው ይህ የንጉሥ አብዱላህ የፋይናንስ ዲስትሪክት ጥቃት ሲደርስበት በዚህ ወር ብቻ ለሁለተኛ ጊዜ ሲሆን፣ ከቀናት በፊትም በሁቲዎች ጥቃት በሳዑዲ አራምኮ ሕንፃ ላይ ተመሳሳይ ጉዳት መድረሱ ይታወሳል።
ይህ ፍንዳታ በሪያድ የተሰማው የሳዑዲ አልጋ ወራሽ መሐመድ ቢን ሳልማን ከአሜሪካ ማዕከላዊ ዕዝ (CENTCOM) አዛዥ አድሚራል ብራድ ኩፐር ጋር በወታደራዊ ግንኙነትና በቀጣናዊ ጉዳዮች ዙሪያ ከተወያዩ ከጥቂት ጊዜ በኋላ መሆኑም ተመላክቷል።
__
ሀሳብ እና’ሳ’ፍራለን
Related Posts
ስፔስኤክስ የመጀመሪያውን የሩብ ዓመት የገቢ ሪፖርት ማቅረቡን ተከትሎ የአክሲዮን ዋጋው በ13 በመቶ ቅናሽ አሳየ
ሐምሌ 30 ቀን 2018 ዓ.ም (መናኸሪያ ሬዲዮ) የኢሎን መስክ ኩባንያ የሆነው ስፔስኤክስ (SpaceX) እንደ ይፋዊ ኩባንያ የመጀመሪያውን የሩብ ዓመት የገቢ... read more
ከመጋቢት ወር ጀምሮ በከተማዋ ወደ 28 የሚደርሱ ሆቴሎች እና ሬስቶራንቶች ማስጠንቀቂያ ተሰጥቷቸዋል ተባለ
በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር፣ ከመጋቢት ወር ጀምሮ ደንብ እና መመሪያ ተላልፈዋል የተባሉ ወደ 28 የሚጠጉ ሆቴሎች ማስጠንቀቂያ እንደተሰጣቸው፣ የከተማ አስተዳደሩ... read more
የታላቁ ህዳሴ ግድብ ፕሮጀክት ያለማንም የውጭ ገንዘብ ድጋፍ እና ብድር በኢትዮጵያዉያን የተሰራ መሆኑ ተገለጸ
ሐምሌ 15 ቀን 2017(መናኸሪያ ሬዲዮ)ታላቁ የአኢትዮጵያ የህዳሴ ግድብ በማህበረሰቡ ተሳትፎ እንጂ የየትኛውም አለም ሀገራት ገንዘብ ያልተካተተበት መሆኑን የህዳሴ ግድብ ማስተባበሪያ... read more
በስልጤ ዞን ሁልባራግ ወረዳ በደረሰ የትራፊክ አደጋ የ8 ሰዎች ህይወት ያለፈ ሲሆን በደብረብርሃን ከተማ በእሳት አደጋ የአንድ የቤተሰብ አባላት የሆኑ ሶስት ሰዎች ህይወት አልፏል ተባለ
በተጨማሪም በሐረር ከተማ ዛሬ ሌሊት 8፡00 ሰዓት ላይ በደረሰ የትራፊክ አደጋ የሁለት ሰዎች ህይወት አልፏል ነው የተባለው
በደብረ ብርሀን ከተማ በደረሰ... read more
ማዕድ ማጋራት የሰው ተኮር እሳቤያችን ተግባራዊ ማሳያ ነው 👉ከንቲባ አዳነች አቤቤ
ማዕድ ማጋራት የሰው ተኮር እሳቤያችን ተግባራዊ ማሳያ ነው ሲሉ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ አዳነች አቤቤ ገለጹ።
ከንቲባዋ በማህበራዊ ትስስር ገጻቸው... read more
በቼክ ሪፐብሊክ ለተሽከርካሪ ወንበር ተጠቃሚዎች ምቹ መንገዶችን የሚያሳይ ካርታ በይፋ ሥራ ላይ ዋለ
ነሐሴ 12 ቀን 2017 (መናኸሪያ ሬዲዮ) የቼክ ሪፐብሊክ መንግስት የአካል ጉዳተኞችን ተንቀሳቃሽነት እና ነጻነት ለማሻሻል ያለመ አዲስ አሰራር በይፋ ተግባራዊ... read more
ባለፉት አምስት አመታት ብልፅግና ያሳካቸውን ድሎች በሁለት እጃችን አፍሰን አንጨርሰውም ሲሉ ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር ዐቢይ አህመድ ተናገሩ
ኅዳር 21 ቀን 2017(መናኸሪያ ሬዲዮ) ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር ዐቢይ አህመድ ብልፅግና ፓርቲ ባለፉት አምስት አመታት ያሳካቸው ድሎች በሁለት እጃችን አፍሰን... read more
ኢራን የራሷን ሳተላይት ወደ ህዋ ማምጠቅ የቻሉ ጥቂት የዓለማችን ሀገራትን ስብስብ ተቀላቀለች፤ የሀገሪቱ የህዋ ቴክኖሎጂ ስኬት ምንድን ነው?
ጥቅምት 28 ቀን 2019(መናኸሪያ ሬዲዮ)ኢራን በራሷ የአገር ውስጥ ቴክኖሎጂ፣ ኢንጂነሪንግ እና ሳይንሳዊ ምርምር ሳተላይት ሰርታ ወደ ህዋ ለማምጠቅ በመቻል በታሪክ... read more
የተዘጋጀው ረቂቅ መመሪያ በቅርብ ወራት ጸድቆ ሲተገበር ደረጃቸውን ያልጠበቁ የማር ምርቶችን ከገበያ እንደሚያስወጣ ተገለጸ
መስከረም 07 ቀን 2019ዓ.ም.(መናኸሪያ ) በማር ምርት ላይ የሚታየውን የጥራት መጓደል፣ ከሌላ ምርት ጋር ቀላቅሎ ለገበያ የማቅረብ ችግር እና ያለ... read more
የቻይና አዲሱ የፍቺ ሕግ፦ የ50/50 የንብረት ክፍፍል ቀርቶ በሰነድ የተረጋገጠ ክፍያ ብቻ እንዲጸድቅ ተወሰነ
መጋቢት 25 ቀን 2018(መናኸሪያ ሬዲዮ) በቻይና በቅርቡ በሥራ ላይ የዋለው አዲሱ የፍትሐ ብሔር ሕግ፣ በትዳር ዘመን የተፈራ ንብረት በፍቺ ወቅት... read more
ምላሽ ይስጡ