
ጥቅምት 30 ቀን 2019(መናኸሪያ ሬዲዮ)አሜሪካ ከኢራን ጋር ለተደረገው ጦርነት ያወጣችውን እያንዳንዱን ወጪ እስራኤል ሙሉ በሙሉ ልትመልስ እንደሚገባ የአሜሪካው ፕሬዚዳንት ዶናልድ ትራምፕ በግልጽ ተናገሩ።
ትራምፕ ከሲቢኤስ «60 ደቂቃዎች» ፕሮግራም ጋር በነበራቸው ቆይታ፣ አሜሪካ ከጎናቸው በመቆም ላደረገችላቸው ጥበቃ የወጣውን ወጪ እነዚያ አገሮች በሙሉ ሊከፍሉን ይገባል ሲሉ አጽንኦት ሰጥተዋል። አክለውም «ወጪውን ሁሉ እስከ መጨረሻዋ ሳንቲም መልሰን እናስገባዋለን» በማለት ያላቸውን ቁርጠኛ አቋም አሳይተዋል።
በንግግራቸውም የእስራኤልን ህልውና ከአሜሪካ ወታደራዊ ድጋፍ ጋር በማያያዝ «ያለ እኛማ በጭራሽ አይኖሩም ነበር፤ ያለ እኛ እስራኤል አትኖርም ነበር» በማለት የብዙዎችን ትኩረት የሳበ ንግግር አሰምተዋል።
__
ሀሳብ እና’ሳ’ፍራለን
ምላሽ ይስጡ