ጥቅምት 11 ቀን 2019(መናኸሪያ ሬዲዮ) በአሁኑ ወቅት በብዙ ከተሞች የሚስተዋለው ከባዱ የኑሮ ውድነት እና የቤት እጥረት በተለይም ተከራዩን ማህበረሰብ ለአስቸጋሪ ኢኮኖሚያዊ ጫና ዳርጎታል።
የቤት ኪራይ ጭማሪን በፐርሰንት (%) ብቻ እንዲሰላ ማድረግ፣ የቤቶቹ መነሻ ዋጋ እጅግ ከፍተኛ በሆነበት ወቅታዊ ሁኔታ አቅምን ፈጽሞ የማይመጥን ወጪ እንዲፈጠር ምክንያት ሆኗል ነው የተባለው።
በዓለም አቀፍ ደረጃ ግን እንደ ጀርመን (በርሊን) እና የአሜሪካ የተወሰኑ ከተሞች (እንደ ኒውዮርክ እና ሳን ፍራንሲስኮ) ያሉ ሀገራት ይህንን ችግር ቀድመው በመረዳት የቤት ኪራይ ዋጋን በቋሚ የገንዘብ መጠን (Fixed Monetary Cap or Rent Control) ይገድባሉ።
እነዚህ ሀገራት አከራዮች ከህጋዊ የዋጋ ሰንጠረዥ ውጭ እንዳያሻቅቡ በቁጥር በመገደብ ተከራዮችን ከከፍተኛ የኢኮኖሚ ጫና ይታደጋሉ።
በዚህም መሠረት በቋሚ የዋጋ ገደብ አሰራር የሚታወቁ ዋና ዋና ሀገራትና ከተሞች የሚከተሉት ናቸው።
1) ጀርመን (በርሊን እና ሌሎች ትልልቅ ከተሞች): በጀርመን ሀገር በተለይም እንደ በርሊን ባሉ ከተሞች የቤት ኪራይ ዋጋን በቁጥር ለመቆጣጠር የሚያስችል ጥብቅ የ«Mietspiegel» (የኪራይ መረጃ ሰንጠረዥ) ሕግ አለ።
ይህ ሰንጠረዥ የቤቱን ስፋት፣ ዕድሜ፣ መሠረተ ልማት እና የሚገኝበትን አካባቢ መሠረት በማድረግ ለሚከራዩ ቤቶች ሊኖር የሚችለውን ከፍተኛ የዋጋ ገደብ በቋሚ የገንዘብ መጠን በግልጽ ያስቀምጣል።
አከራዮች ከዚህ ሕጋዊ ሰንጠረዥ ውጭ ዋጋ ጨምሮ ማከራየት በጥብቅ የተከለከለ ነው።
2) ዩናይትድ ስቴትስ (ኒውዮርክ እና ሳን ፍራንሲስኮ): በአሜሪካ ውስጥ እንደ ኒውዮርክ ከተማ እና ሳን ፍራንሲስኮ ያሉ አካባቢዎች የ«Rent Control» እና የ«Rent Stabilization» ሕጎችን በስራ ላይ ያውላሉ።
እነዚህ ሕጎች አከራዮች በየዓመቱ በዘፈቀደ ወይም በፐርሰንት ከፍ ያለ ጭማሪ እንዳያደርጉ ይገድባሉ። በምትኩ በመንግስት በሚወጣ ቋሚ የዋጋ መጠን እና በዋጋ ንረት (Inflation) ልክ ብቻ እንዲጨምር ይደረጋል።
በአጠቃላይ እነዚህ ሀገራት የቤት ኪራይን በቋሚ የዋጋ ሰንጠረዥ በመምራት ተከራዮች ከግል አከራዮች የዘፈቀደ የዋጋ ጭማሪ እንዲጠበቁ እና ፍትሃዊ የኑሮ ማዕቀፍ እንዲኖራቸው አድርገዋል።
__
ሀሳብ እና’ሳ’ፍራለን
ምላሽ ይስጡ