መስከረም 11 ቀን 2019 ዓ.ም (መናኸሪያ ሬዲዮ) በየመን ለሚገኙ ትውልደ ኢትዮጵያውያን አስፈላጊው ክትትል እየተደረገ መሆኑን የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ለመናኸሪያ ሬዲዮ አስታውቋል፡፡ በየመን መንግሥት ኃይሎችና በኢራን በሚደገፉት የሑቲ ታጣቂዎች መካከል እየተካሄደ ባለው ውጊያ በርካታ ዜጎች ከየመን ወደ ጅቡቲ እየተሰደዱ መሆናቸውን የሚወጡ መረጃዎች አመልክተዋል። የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት የስደተኞች ኤጀንሲ መረጃም በሀገሪቱ ከሚገኙና ከተመዘገቡ ስደተኞች መካከል ትውልደ ኢትዮጵያውያን በርካታ እንደሆኑ ገልጿል። በውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር የመካከለኛው ምስራቅ፣ የእስያና ፓሲፊክ ሀገራት ጉዳዮች ዳይሬክተር አምባሳደር ደዋኖ ከድር ሚኒስቴሩ በየመን በሥጋት ውስጥ የሚገኙ ትውልደ ኢትዮጵያውያንን ጉዳይ በቅርበት እየተከታተለ መሆኑን አስታውቀዋል፡፡ በአካባቢው ያለው ሁኔታ አስቸጋሪ ቢሆንም በተቻለ መጠን ለዜጎች ለመድረስ እየተሞከረ መሆኑን ተናግረዋል፡፡ በተለይም በዜጎች ላይ ጉዳት እንዳይደርስባቸው ባሉበት እንዲቆዩና እንቅስቃሴ እንዳያደርጉ የማድረግ፣ እንዲሁም ድጋፍ እንዲያገኙ ከሚመለከታቸው አካላት ጋር በመተባበር እየተሠራ መሆኑን አምባሳደሩ ገልጸዋል፡፡ በየመን የሚገኙ የተወሰኑ ነዋሪዎችን በሚኒስቴሩ በኩል እንደሚያገኟቸው የተናገሩት አምባሳደር ደዋኖ፣ ሌሎቹንም ያሉበትን ሁኔታ ለማረጋገጥ ጥረት እየተደረገ እንደሚገኝ አመልክተዋል፡፡ በየመን እየተካሄደ ባለው ጦርነት በርካታ ዜጎች በቀይ ባሕር በኩል ወደ ጅቡቲ እየገቡ መሆኑን መረጃዎች ያመለክታሉ። ___ ሀሳብ እና‘ሳ‘ፍራለን
Related Posts
የገዛ ልጃቸውን ለህክምና ወጪ የሸጡት አባት ልብ ሰባሪ ታሪክ
ግንቦት 12 ቀን 2018(መናኸሪያ ሬዲዮ) በአፍጋኒስታን የሚገኘው ከፍተኛ የኢኮኖሚ ቀውስ እና ስራ አጥነት ወላጆችን አስገዳጅ እና ልብ ሰባሪ ውሳኔዎች ላይ... read more
አፍሪካ በሁሉም መስክ ከተረጂነት ወጥታ ራሷን ለመቻል ጥረት ማድረግ ይገባታል ተባለ
ጥር 16 ቀን 2017(መናኸሪያ ሬዲዮ)አሜሪካ ከአለም የጤና ድርጅት አባልነት እንደምትወጣ ማስታወቋን ተከትሎ ውሳኔዋ የአለምን ብሎም የአፍሪካን የጤና ችግር ሊጎዳው እንደሚችል... read more
ግዙፍ የሆኑ የከተማዋ ሞሎች እና ሪል-ስቴቶች የአከራይ ተከራይ ግብር እየከፈሉ አለመሆኑን የአዲስ አበባ ገቢዎች ቢሮ አስታወቀ
ታኅሳስ 15 ቀን 2017(መናኸሪያ ሬዲዮ) በከተማዋ የሚገኙ የጋራ መኖሪያ ቤቶች ግዙፍ ህንጻ የሚያከራዩ እና ሪል-ስቴት ባለቤቶች የአከራይ ተከራይ ግብር እንዲከፍሉ... read more
የኤሌክትሪክ መኪናዎን ባትሪ ሳያውቁት እየጎዱት ይሆን?እንዳይበላሽብዎ ማወቅ ያለብዎት 4 ወሳኝ ሚስጥሮች!
ጥቅምት 28 ቀን 2019(መናኸሪያ ሬዲዮ) በአሁኑ ጊዜ በመንገዶቻችን ላይ የኤሌክትሪክ መኪኖች (EVs) በብዛት ማየት የተለመደ ሆኗል።
የኤሌክትሪክ መኪና ሲኖረን የነዳጅ መኪና... read more
42ኛ መደበኛ የሚኒስትሮች ምክር ቤት ስብስባ ውሳኔዎች
🔰የሚኒስትሮች ምክር ቤት በዛሬው ዕለት ባካሄደው 42ኛ መደበኛ ስብሰባ በተለያዩ ጉዳዮች ላይ ተወያይቶ ውሳኔ አሳለፈ፡፡
1.በቅድሚያ ምክር ቤቱ የተወያየው የኢትዮጵያ የአደጋ... read more
ከዛሬ ታህሳስ 23 ቀን 2017 ዓ.ም ጀምሮ በአዲስ አበባ በሚገኙ በሁሉም ባንኮች አዲስ የባንክ ሒሳብ ለመክፈት የፋይዳ ዲጂታል መታወቂያ (የፋይዳ ቁጥር) ይዞ መቅረብ ግዴታ መሆኑ የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ ገልጿል፡፡
ሀሳብ እና'ሳ'ፍራለን
መናኸሪያ ሬዲዮ 99.1
ሃሳብ፣አስተያየት እና ጥቆማ ለመስጠት የሚከተሉትን የስቱዲዮ ስልኮቻችን ይጠቀሙ
👉011-639-28-52👉011-639-37-63
የቀጥታ ስርጭት 👉 📻 (https://worldradiomap.com/et/play/menaharia) radio 99.1 (https://stream.zeno.fm/yw8poig9iwtuv)
✅ https://t.me/menaharia_fm
✅https://x.com/MenahriaFm99_1
ትክክለኛውን የመናኸሪያ... read more
ኢምባሲዎች የየሀገራቸውን ባህል በማስተዋወቅ የፌስቲቫሉ አካል እንዲሆኑ እየሰሩ እንደሚገኙ የጳጉሜን ፌስቲቫል አዘጋጆች ገለጹ
ነሐሴ 30 ቀን 2018(መናኸሪያ ሬዲዮ) ኢምባሲዎች የየሀገራቸውን ባህል በማስተዋወቅ የፌስቲቫሉ አካል እንዲሆኑ እየሰሩ እንደሚገኙ የጳጉሜን ፌስቲቫል አዘጋጆች ለመናኸሪያ ሬዲዮ አስታወቁ።... read more
የኢትዮጵያ አየር መንገድ ያወጣው መግለጫ
መስከረም 13 ቀን 2019 ዓ.ም (መናኸሪያ ሬዲዮ) የኢትዮጵያ አየር መንገድ በትግራይ ክልል ባለው ወቅታዊ ሁኔታ ምክንያት ወደ መቐለ፣ አክሱምና ሽሬ... read more
ፕሬዝዳንት ዘለንስኪ በአሜሪካ የሚደገፈውን የሰላም ስምምነት ለመፈረም ዝግጁ አይደሉም ተባለ
ሕዳር 29 ቀን 2018(መናኸሪያ ሬዲዮ) የአሜሪካ ፕሬዝዳንት እና የሪፐብሊካን እጩ ዶናልድ ትራምፕ፣ የዩክሬኑ ፕሬዝዳንት ቮሎዲሚር ዘለንስኪ በሁለቱ ሀገራት መካከል ያለውን... read more
ሶስት ተቋማት በቱሪዝም ዘርፍ በትብብር ለመስራት ተፈራረሙ
የኢትዮጵያ አየር መንገድ፣ የኢሚግሬሽንና ዜግነት አገልግሎት እና የቱሪዝም ሚኒስቴር በቱሪዝም ዘርፍ በትብብር መስራት የሚያስችላቸውን የመግባቢያ ሰነድ ዛሬ ተፈራርመዋል።
ስምምነቱን የተፈራረሙት የኢትዮጵያ... read more
ምላሽ ይስጡ