መጋቢት 25 ቀን 2018(መናኸሪያ ሬዲዮ)ቢሮው በመካከለኛው ምስራቅ በተከሰተው ቀውስ ምክንያት ሊያጋጥም የሚችለውን የነዳጅ እጥረት ለመከላከልና ስርጭቱን በሥርዓት ለመምራት እንዲቻል፣ በነዳጅ ማደያዎች ቅድሚያ አገልግሎት የሚሰጣቸውን ተቋማት ዝርዝር ይፋ አድርጓል። በዚህም መሰረት ለነዳጅ አጓጓዥ ተሽከርካሪዎች ወይም ቦቴዎች፣ ለከፍተኛ አምራች ኢንዱስትሪዎች በተለይም መሰረታዊ የምግብ ፍጆታና የኤክስፖርት ምርቶችን ለሚያመርቱ ተቋማት ቅድሚያ ይሰጣል።
በተጨማሪም ግንባታ ላይ ላሉና ትኩረት ለሚሰጣቸው የመንግስትና የግል ፕሮጀክቶች፣ ለደረቅ ጭነት እና ለግንባታ ቁሳቁስ አጓጓዥ ተሽከርካሪዎች እንዲሁም ገበያ ለማረጋጋት የግብርናና የኢንዱስትሪ ፍጆታ ምርቶችን ለሚያጓጉዙ ተሽከርካሪዎች አገልግሎቱ በቅድሚያ እንደሚሰጥ ተገልጿል። ለግብርና ማሽነሪዎችና ትራክተሮች፣ ለሀገር አቋራጭ የሕዝብ ማመላለሻዎች እንዲሁም ለከተማ የሕዝብ ትራንስፖርት አገልግሎት ሰጪ ተሽከርካሪዎችም በተመሳሳይ ቅድሚያ ተሰጥቷቸዋል።
ለሕብረተሰብ አገልግሎት ሰጪ የሆኑት አምቡላንሶች፣ ቀዶ ጥገና የሚያከናውኑ የጤና ተቋማት፣ የኤሌክትሪክ አገልግሎት ሰጪዎችና ሌሎች እንደ አስፈላጊነቱ በንግድ ቢሮው እየቀረቡ በግብረ ኃይል ውሳኔ የሚሰጥባቸው ተቋማትም የቅድሚያ ተጠቃሚ እንደሚሆኑ ቢሮው አስታውቋል። ይህ ውሳኔ የከተማዋን መሰረታዊ እንቅስቃሴዎች ሳይስተጓጎሉ ለማስቀጠል ያለመ መሆኑ ተመላክቷል።
__
ሀሳብ እና’ሳ’ፍራለን
ምላሽ ይስጡ