መጋቢት 09 ቀን 2018(መናኸሪያ ሬዲዮ)በሌላ በኩል አስቻይ ሁኔታ ባለባቸው አካባቢዎች ማህበረሰቡን ለማንቃት የተለያዩ ተግባራትን እያከናወኑ መሆኑን ቪዥን ኢትዮጵያ እና የኢትዮጵያ ሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶች ለመናኸሪያ ሬድዮ አስታውቀዋል።
ካለፉት የምርጫ ኩነቶች አንጻር በጸጥታ ችግር እና ከግብረሰናይ ድርጅቶች የሚገኘው የገንዘብ ድጋፍ በመቋረጡ ምክንያት የሰባተኛው አገራዊ ምርጫ ለሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶች ፈታኝ እንደሆነ የቪዥን ኢትዮጵያ መስራችና ዳይሬክተር አቶ ታደለ ደርሰ ተናግረዋል።
በተለያዩ አካባቢዎች ባሉ የጸጥታ ችግሮች ምክንያት ተንቀሳቅሶ የግንዛቤ ማስጨበጥ ሥራ ለመሥራት አስቻይ ሁኔታ እንደሌለ የሚናገሩት ዳይሬክተሩ፤ እነዚህ ችግሮች ቢቀረፉ በሁሉም አካባቢ ተንቀሳቅሶ መሥራት እንደሚቻል አንስተዋል። የጸጥታ ስጋት በሌለባቸው አካባቢዎች ድርጅታቸው ማህበረሰቡን የማንቃት እና የስነ-ምርጫ ትምህርት ከምርጫ ቦርድ ጋር በመሆን በጋራ እየሰጠ መሆኑንም ገልጸዋል።
የኢትዮጵያ ሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶች የምርጫ ዋና ዳይሬክተር አቶ አበራ ሃይለማርያም በበኩላቸው፤ የምርጫ ትምህርት፣ የምርጫ ታዛቢነት እና የመገናኛ ብዙሃን ምህዳርን የሚመለከቱ ሥራዎች እየተሰሩ መሆኑን ተናግረዋል።
አሁን ላይ መራጮች እንዲመዘገቡ እና ስለ ምርጫው ግንዛቤ እንዲኖራቸው ድርጅታቸው በተለያዩ የሀገሪቱ ክፍሎች ተንቀሳቅሶ እየሰራ መሆኑን ጠቅሰው፤ በተለያዩ አካባቢዎች ላይ ለሚስተዋሉ የጸጥታ ችግሮች መንግስት ትኩረት ሊሰጥ እንደሚገባ አሳስበዋል።
በመጨረሻም በኢትዮጵያ አንዳንድ አካባቢዎች የሚስተዋሉትን የጸጥታ ችግሮች ለመፍታት መንግስት እና ባለድርሻ አካላት ድርሻቸውን እንዲወጡ የሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶቹ ጥሪያቸውን አቅርበዋል።
__
ሀሳብ እና’ሳ’ፍራለን
ምላሽ ይስጡ