ጥር 05 ቀን 2018(መናኸሪያ ሬዲዮ) ይህ የተገለጸው በጃፓን የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ሚኒስትር ዴኤታ በተመራውና ከ40 ኩባንያዎች የተውጣጡ 48 ተወካዮችን ባቀፈው ልዑክ እና በኢትዮጵያ መካከል የሁለትዮሽ የኢኮኖሚ ፎረም በተካሄደበት መድረክ ላይ ነው።
የሁለቱን ሀገራት የንግድ ግንኙነት ለማጠናከር ያለመው ይህ የቢዝነስ ፎረም፤ በቴክኖሎጂ ሽግግር፣ በሰው ኃይል ስልጠና፣ በአዳዲስ የገበያ መዳረሻዎች እና አማራጮች ዙሪያ ከንግድና ቀጠናዊ ትስስር ሚኒስቴር፣ ከኢንቨስትመንት ኮሚሽን እና ከውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ጋር ሰፊ ውይይት አድርጓል።
የንግድና ቀጠናዊ ትስስር ሚኒስትሩ አቶ ካሳሁን ጎፌ በፎረሙ ላይ ባደረጉት ንግግር፣ ኢትዮጵያ በአፍሪካ አህጉራዊ ነፃ የንግድ ቀጠና ማዕቀፍ ስር የንግድ ልውውጥን በይፋ መጀመሯ ለሁለትዮሽ የኢኮኖሚ ትብብሩ ያለው ጠቀሜታ ከፍተኛ መሆኑን ገልጸዋል።
ሚኒስትሩ አክለውም የጃፓን ኩባንያዎች 1.4 ቢሊዮን ሕዝብ የሚኖርበትን ሰፊ የአፍሪካ ገበያ ከኢትዮጵያ በመነሳት እንዲያገኙ ይህ ትብብር ሰፊ በር የሚከፍት መሆኑን አስረድተዋል።
ሚኒስትሩ በመድረኩ ላይ እንዳብራሩት፣ ባለፉት አምስት ዓመታት ማለትም ከ2020-2024 አማካይ ዓመታዊ የንግድ ልውውጡ 478 ሚሊዮን ዶላር የደረሰ ሲሆን፤ በ2024 የታየው የ307.2 ሚሊዮን ዶላር የንግድ ልውውጥ ደግሞ የሁለቱን ሀገራት የንግድ ትስስር ዘላቂነት የሚያሳይ መሆኑን ጠቁመዋል።
የቴሌግራም ቻናላችን ይቀላቀሉ 👉 https://t.me/menaharia_fm
__
ሀሳብ እና’ሳ’ፍራለን 📞
👉011-639-28-52
👉011-639-37-63 (https://stream.zeno.fm/yw8poig9iwtuv)
ምላሽ ይስጡ