ታህሳስ 15 ቀን 2018(መናኸሪያ ሬዲዮ) በእንግሊዝ በሚገኝ አንድ የእንስሳት ማቆያ ውስጥ የሚገኙ አምስት የአፍሪካ ግራጫ በቀቀኖች ወደ ስፍራው የሚመጡ ጎብኚዎችን ባለጌ ቃላትን በመጠቀም ሲሳደቡ በመገኘታቸው ከእይታ እንዲርቁ ተደረገ።
እነዚህ በቀቀኖች እርስ በርስ እየተበረታቱ ጎብኚዎችን መሳደብና መሳለቅ የጀመሩ ሲሆን፣ ድርጊታቸው እየባሰ በመሄዱ የእንስሳት ማቆያው ጠባቂዎች በቀቀኖቹን ለይተው ለማስቀመጥ ተገደዋል። ጠባቂዎቹ እንደሚሉት ከሆነ፣ በቀቀኖቹ ስድቦቹን የተማሩት ከሰዎች ሲሆን፣ አንዱ ሲሳደብ ሌላኛው በመሳቅና በማበረታታት ድርጊቱን ለየት ያለ ጨዋታ አስመስለውት ነበር።
የእንስሳት ማቆያው ኃላፊዎች በቀቀኖቹን ለጊዜው ከሰው እይታ አርቀው ለብቻቸው ያስቀመጧቸው ሲሆን፣ ዓላማውም በቀቀኖቹ እርስ በርስ የሚለዋወጡትን መጥፎ ቃላት ረስተው የተሻሉ ቃላትን እንዲለምዱ ለማድረግ ነው። ይህ ያልተለመደ ክስተት በማህበራዊ ሚዲያ ላይ መነጋገሪያ ሆኗል።
ምላሽ ይስጡ