ታህሳስ 15 ቀን 2018(መናኸሪያ ሬዲዮ)በፈረንሳይ አንድ የ9 ዓመት ታዳጊ ህጻን ለሁለት ዓመታት ያህል ያለምንም ተንከባካቢ በአፓርታማ ውስጥ ብቻውን መኖሩ ተሰማ። ህጻኑ በዚህ ሁሉ ጊዜ ውስጥ ሙቀት፣ ሙቅ ውሃ እና በቂ ምግብ ባልነበረበት ሁኔታ ውስጥ የቆየ ሲሆን፣ በሚገርም ሁኔታ ግን በየቀኑ ትምህርት ቤት በመሄድ ጎበዝ ተማሪ ሆኖ ቀጥሏል።
የህጻኑ እናት ከአዲሱ የፍቅር አጋሯ ጋር 5 ኪሎ ሜትር ብቻ ርቃ በሌላ ቤት ስትኖር፣ ልጇ ግን ኬክ፣ የታሸጉ ምግቦችንና ከጎረቤት አትክልት ስፍራ ቲማቲሞችን እየሰረቀ በመብላት ለብቻው ተርፏል። ይህ እጅግ አስደንጋጭ ታሪክ ሊታወቅ የቻለው፣ እናትየው በ2022 ለምግብ እርዳታ ወደ ማህበራዊ አገልግሎት ተቋማት ባቀናችበት ወቅት በተደረገ ማጣራት ነው።
በዚህ ሳምንት የፈረንሳይ ፍርድ ቤት እናትየው በፈጸመችው ከፍተኛ የቸልተኝነት ወንጀል የ18 ወራት እስራት እንዲፈረድባት ወስኗል። ይህ ክስተት “ሁሉንም ነገር በትክክል ለሚያደርጉ እና ጥሩ ለሚመስሉ ህጻናት ማን ትኩረት ይሰጣል?” የሚል ጥያቄን በማህበራዊ ሚዲያ ላይ አስነስቷል።
ምላሽ ይስጡ