የተባበሩት መንግሥታት የኤድስ መከላከል ፕሮግራም (ዩኤንኤድስ) ዓለም አቀፍ የኤድስ ቀንን አስመልክቶ ይፋ ባደረገው የ2025 ሪፖርት፣ በኤድስ የሚያዙ ሰዎች ቁጥር ከ2010 ወዲህ እየቀነሰ ቢመጣም፣ ከሰሃራ በታች ባሉ የአፍሪካ ሀገሮች የሚገኙ ታዳጊና ወጣት ሴቶች ከቀረው ዓለም ጋር በማይመጣጠን መልኩ ለበሽታው ተጋላጭ መሆናቸውን ገልጿል።
ሪፖርቱ እንደሚያመለክተው፣ በኤድስ ከሚያዙ ሰዎች መካከል 25 በመቶውን የሚይዙት ከእነዚህ ታዳጊና ወጣት ሴቶች ናቸው።
በተለይም ከ15 እስከ 24 ባለው የዕድሜ ክልል ውስጥ ያሉ ወንዶች በኤድስ የመያዝ ሁኔታቸው በ62 በመቶ ሲቀንስ፣ በተመሳሳይ የዕድሜ ክልል ውስጥ የሚገኙ ሴቶች በኤድስ የመያዝ ሁኔታቸው የቀነሰው በ51 በመቶ ብቻ ነው። ይህም በሴቶችና በወንዶች መካከል ያለውን ከፍተኛ ልዩነት ያሳያል።
በ2024 ዓ.ም. በዓለም አቀፍ ደረጃ በቀን 570 አዳዲስ ታዳጊና ወጣት ሴት የኤድስ ታማሚዎች ተመዝግበዋል።
እንደ ሪፖርቱ ከሆነ፣ እ.ኤ.አ. ከ2010 እስከ 2024 ባለው ጊዜ ውስጥ በተሰሩ ሥራዎች ምክንያት ከ15 እስከ 24 የዕድሜ ክልል ውስጥ ያሉ ታዳጊና ወጣት ሴቶች በኤድስ የመያዝ ምጣኔ በዓለም አቀፍ ደረጃ በግማሽ ያህል መቀነስ ችሎ ነበር።
በዛሬው የጤናማሕይወት ዝግጅታችንም ኤች አይ ቪ ኤድስን በተመለከተ ሰፋ ያለ ትኩረት ሰጥተናል። ባልደረባችን ማህሌት ሙሉጌታ ከጤና ባለሙያ ጋር ባደረገችው ቆይታ ዝርዝር መረጃዎችን አሰናድታለች።
ምላሽ ይስጡ