ሕዳር 17 ቀን 2018(መናኸሪያ ሬዲዮ) ከህዳር 5/ 2018 ዓ.ም ጀምሮ የማርበርግ ህክምና ምርመራ ሲደረግ የቆየ ሲሆን በበሽታው ከተጠቁ 11 ሰዎች 6ቱ ህይወታቸው ማለፉን የጤና ሚኒስትር ዶክተር መቅደስ ዳባ ተናግረዋል።
በሽታው መከሰቱ ከተገለጸበት ቀን አንስቶ እስካሁን ለ73 ሰዎች የላብራቶሪ ምርመራ የተከናወነ መሆኑን ያነሱት ሚኒስትሯ፡ ቫይረሱ በ11 ሰዎች ላይ መገኘቱና 6ቱ ህይወታቸው ማለፉን ገልጸዋል።
በተጨማሪም ቫይረሱ ተገኝቶባቸው ህይወታቸው ካለፉ ውጪ 5 ሰዎች ደግሞ በህክምና ላይ እንደሚገኙ አንድ ጽኑ ታማሚ መኖሩ ጠቁመዋል።
ከታማሚዎች ጋር ንክኪ ከነበራቸው 3መቶ 49 ሰዎች ወስጥ 1መቶ 19ኙ ነጻ ሲሆኑ ቀሪ 2መቶ 30ዎቹ በለይቶ ክትትል ላይ እንደሚገኙ ዶክተር መቅደስ አክለዋል።
ቫይረሱ መከሰቱን ተከትሎ በጤና ሚኒስትር ዶክተር መቅደስ ዳባ የሚመራ ሀገር አቀፍ ግብረ ኃይል መቋቋሙን አስታውሰው፤ ግብረ ኃይሉ በየቀኑ በሽታው ያለበትን ደረጃ በተመለከተ ግምገማ እያካሄደ እንደሚገኝ አብራርተዋል።
የቴሌግራም ቻናላችን ይቀላቀሉ 👉 https://t.me/menaharia_fm
__
ሀሳብ እና’ሳ’ፍራለን 📞
👉011-639-28-52
👉011-639-37-63 (https://stream.zeno.fm/yw8poig9iwtuv)
ምላሽ ይስጡ