ሕዳር 17 ቀን 2018(መናኸሪያ ሬዲዮ)በአሜሪካ የሚገኘው ታላቁ የኒው ዮርክ ከተማ በየዓመቱ ቀስ በቀስ እየሰጠመ መሆኑን የሚያሳይ አዲስ አስደንጋጭ ጥናት በቅርቡ በ Earth’s Future በተባለው ሳይንሳዊ መጽሔት ላይ ታትሟል። ተመራማሪዎቹ ከተማዋ እየሰጠመች መሄዷ ዋናው ምክንያት ደግሞ እጅግ በጣም ግዙፍ የሆኑት ሰማይ ጠቀስ ህንጻዎች ክብደት እንደሆነ ገልጸዋል።
ሳይንቲስቶች እንደሚሉት፣ ከተማዋ በአማካይ በየዓመቱ ከ 1 እስከ 2 ሚሊ ሜትር እየሰጠመች ትገኛለች። በአንዳንድ ደካማ አፈር ላይ የተገነቡ አካባቢዎች ግን ይህ መጠን በሁለት እጥፍ ሊጨምር እንደሚችል ጥናቱ ያመለክታል።
ይህ ቀስ በቀስ የመሬት መሰርሰር ከባሕር ወለል መጨመር ጋር ተደምሮ ለአደጋ የሚያጋልጥ ሆኗል። ከ1950 ዓ.ም ወዲህ ብቻ የአካባቢው የውኃ መጠን በ 22 ሴንቲ ሜትር ያህል ጨምሯል። የመሬት መሰርሰር፣ የባሕር ወለል መጨመር እና በየጊዜው የሚከሰቱ ኃይለኛ አውሎ ነፋሶች ተደማምረው በከተማዋ ላይ የሚደርሰውን ዋና ዋና የጎርፍ አደጋዎች ቁጥር በእጅጉ እንደሚያበዙት ባለሙያዎቹ አስጠንቅቀዋል።
ሳይንቲስቶቹ አክለውም፣ ተደጋጋሚ የጨው ውኃ ንክኪ በህንጻዎች ውስጥ ያሉትን የብረት ምሰሶዎች ሊያበላሽ፣ ሕንፃዎችን ሊያዳክም እንዲሁም በከተማዋ ለሚኖሩት 8.4 ሚሊዮን ነዋሪዎች የደህንነት ስጋት መፍጠር እንደሚችል አስጠንቅቀዋል።
የቴሌግራም ቻናላችን ይቀላቀሉ 👉 https://t.me/menaharia_fm
__
ሀሳብ እና’ሳ’ፍራለን 📞
👉011-639-28-52
👉011-639-37-63 (https://stream.zeno.fm/yw8poig9iwtuv)
ምላሽ ይስጡ