ሕዳር 15 ቀን 2018(መናኸሪያ ሬዲዮ)የአሜሪካን አህጉር ከምዕራብ ዳርቻ (ፓሲፊክ ውቅያኖስ) ወደ ምሥራቅ ዳርቻ (አትላንቲክ ውቅያኖስ) የሚያገናኘው አስደናቂ የባቡር ጉዞ ርዝመትና ዋጋ ይፋ ሆኗል።
በአገሪቱ ካሉ እጅግ ማራኪ የጉዞ መስመሮች አንዱ የሆነው ይህ ታሪካዊ ጉዞ በጠቅላላ 5,467 ኪሎ ሜትር ርዝመት ያለው መስመር ይሸፍናል። ባቡሩ በጉዞው ላይ በአጠቃላይ 11 የአሜሪካ ግዛቶችን ያቋርጣል። ጉዞው በዋነኝነት ከፓሲፊክ ዳርቻ (በካሊፎርኒያ አካባቢ) ተነስቶ አገሪቱን አቋርጦ አትላንቲክ ዳርቻ ወደምትገኘው ኒው ዮርክ ከተማ ያደርሳል።
ባቡሩ በበረሃማ ሜዳዎች፣ በድንቅ ተራራማ አካባቢዎች እና በትላልቅ ከተሞች ውስጥ የሚያልፈው አስገራሚ የተፈጥሮ ገጽታ የዓለምን ትኩረት ስቧል።
ለዚህ ረጅም እና አስደናቂ ጉዞ ለመጀመሪያ ጊዜ የሚቀርበው (የተቀነሰው) የመንገደኛ ትኬት ዋጋ ከ213 ዶላር ጀምሮ መሆኑ ተገልጿል።
ምላሽ ይስጡ