ኅዳር 10 ቀን 2018 (መናኸሪያ ሬዲዮ) ኤጀንሲው በሰው ሠራሽ አስተውሎት የለማ መተግበሪያ አሠራሩን ለማዘመን ከሁለት ዓመት በላይ ሲሠራ መቆየቱንና አሁን ላይ በሙከራ ሂደት ላይ እንደሚገኝ ለመናኸሪያ ሬዲዮ አስታውቋል።
ኤጀንሲው በተደጋጋሚ የሚያጋጥመው የሥርዓት (ሲስተም) መቆራረጥ ችግር ፈተና ሆኖበት እንደቆየ የሚገልጹት የኤጀንሲው ምክትል ዋና ዳይሬክተር አቶ ጥጋቡ ሹመይ፤ ኤጀንሲው አሁን ላይ በሰው ሠራሽ አስተውሎት የለማ አዲስ መተግበሪያን ወደ ሥራ አስገብቶ በሙከራ ላይ እንደሆነ ተናግረዋል።
አዲሱ ሥርዓት ከዚህ ቀደም ማኅበረሰቡ ያነሳቸው የነበሩ ቅሬታዎችን ለማስተካከል እንደሚረዳ የተናገሩት ምክትል ዋና ዳይሬክተሩ፤ አሁን ላይ የበለጸገው ሥርዓት ሙከራ ላይ እንደሆነና እስከ ኅዳር መጨረሻ ድረስ ሙሉ ለሙሉ ተግባራዊ እንደሚደረግ ገልጸዋል።
አሁን ላይ ኤጀንሲው እየተጠቀመበት ያለው መተግበሪያ ለ14 ዓመታት አገልግሎት የሰጠ መሆኑን የሚገልጹት አቶ ጥጋቡ፤ ብልሹ አሠራር እና የሐሰተኛ ሰነድ ስርጭትን ለማስቀረት ከተለያዩ ባለድርሻ አካላት ጋር እየተሠራበት እንደሆነ አብራርተዋል።
የኤጀንሲው እና የሰው ሠራሽ አስተውሎት ባለሙያዎች በጋራ በመሆን አዲሱን መተግበሪያ የማረጋገጥ ሥራ እየሠሩ መሆኑን አቶ ጥጋቡ አመላክተዋል።
የቴሌግራም ቻናላችን ይቀላቀሉ 👉 https://t.me/menaharia_fm
__
ሀሳብ እና’ሳ’ፍራለን 📞
👉011-639-28-52
👉011-639-37-63 (https://stream.zeno.fm/yw8poig9iwtuv)
ምላሽ ይስጡ