ሕዳር 05 ቀን 2018(መናኸሪያ ሬዲዮ) የቡና ከረጢቶችን የፈጠራ አቅም ከባንግላዲሽ መማር እንደሚያስፈልግ በንግድና ቀጠናዊ ትስስር ሚኒስትር ዴኤታ አቶ ይድነቃቸው ወርቁ ተናግረዋል።
ባንግላዲሽ ከቃጫ መሰል ግብዓት የሚሰራ ታዋቂ የቡና ከረጢት እንዳላቸውና ለተለያዩ ቡና አምራችና ላኪ ሀገራት እንደሚያቀርቡ ሚኒስትር ዴእታው ተናግረዋል።
የራሳችንን እምቅ አቅም ለመጠቀም የተለየ የፈጠራ ሂደትን መከተል የኢትዮጵያ የለውጥ ስራ አንዱ አካል ነው ያሉት ሚኒስትር ዴእታው ከተለያዩ ሀገራት ልምድ ለመውሰድም እየተደረጉ ያሉት አለም አቀፍ የንግድ ትስስር ሂደቶች እድል እንደሚፈጥሩ ገልጸዋል።
ኢትዮጵያ ለአለም የንግድ ድርጅት አባልነት ላለፉት 22 አመታት ስትሞክር መቆየቷን የገለጹት ሚኒስትር ዴእታው ላለፉት አምስት አመታት በተለይም ከማክሮ ኢኮኖሚው ማሻሻያ ማግስት ኢትዮጵያ ይበልጥ ግፊት እያደረገች መሆኑን ተናግረዋል። ለዚህ አይነቱ አጋዥ ሂደቶች ከሀገራት ጋር የሚደረጉት የንግድ ልምድ ልውውጥና ትስስር የዲፕሎማሲ ሂደቶች ናቸውም ሲሉ አክለዋል።
ኢትዮጵያ እየተገበረች ለምትገኘው ዘርፈ ብዙ የለውጥ ሂደት በተለይ በንግድና ኢንቨስትመንት ዘርፍ ያለው የሀገራት ትስስር አመርቂ ውጤት እያሳየ መሆኑንንም ሚኒስትር ዴእታው ገልጸዋል።
የቴሌግራም ቻናላችን ይቀላቀሉ 👉 https://t.me/menaharia_fm
__
ሀሳብ እና’ሳ’ፍራለን 📞
👉011-639-28-52
👉011-639-37-63 (https://stream.zeno.fm/yw8poig9iwtuv)
ምላሽ ይስጡ