ሕዳር 05 ቀን 2018(መናኸሪያ ሬዲዮ) የትምህርት ሚኒስቴር ባለፈው ዓመት ጀምሮ በሃገሪቱ ያሉ ሁሉም ከፍተኛ የትምህርት ተቋማት ለተማሪዎቻቸው የሚያቀርቡት የምግብ አይነት ተመሳሳይ እንዲሆን ማድረጉ የሚታወስ ነው፡፡
የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ተመሳሳይ የተደረገው የምግብ ዝርዝር በኢትዮጵያ ተማሪዎች ህብረት በኩል እንዲሁም በትምህርት ሚንስቴር በኩል ተጠይቆ የተወሰነ እንደሆነ በአዲግራት ዩኒቨርሲቲ የኮምዩኒኬሽን ዳይሬክተር አቶ ዮሐንስ ከበደ ለጣቢያችን ገልጸዋል፡፡
በዩኒቨርሲቲዎች ከዚህ ቀደም የነበረው የምግብ ዝርዝር 22 ብር የነበረ እንደሆነ ያመላከቱት አቶ ዮሐንስ፣ ከባለፈው አመት ጀምሮ 100 ብር መደረጉ የተወሰኑ መሻሻሎች እንዳሉት ገልጸዋል፡፡
ነገር ግን ተመሳሳይ ሲደረግ በአካባቢው የሌሉ የምግብ አይነቶችን ለማካተት አስቸጋሪ እንደሆነ ገልጸው፣ ዩኒቨርሲቲው የሌሎች ዩኒቨርስቲዎችን ተሞክሮ በመውሰድ በሌላ የምግብ አይነት የመተካት ስራ እንደሰራ ገልፀዋል፡፡
አክለውም በየአመቱ የሚታየው የዋጋ ንረት ዩኒቨርሲቲው ከሚቀበላቸው ተማሪዎች ቁጥር አንፃር ሲታይ ግን አሁንም ፈታኝ ሁኔታ እንዳለም አመላክተዋል፡፡
በዩኒቨርሲቲው ውስጥ ይፈጠር የነበረውን የበጀት እጥረት የፈታ እንደሆነና ጥሩ አፈጻጸም እንደነበራቸው የገለፁት የወላይታ ሶዶ ዩኒቨርሲቲ ፕሬዝዳንት ዶክተር ጉቼ ጉኔ፣ የመመገቢያ ዝርዝሩ ተመሳሳይ ከመደረጉ በፊት ዩኒቨርሲቲው የበጀት እጥረት ያጋጥመው እንደነበር ተናግረዋል፡፡
በተማሪዎች ጥያቄና በትምህርት ሚንስቴር በኩል በተደረገው ስምምነት መሰረት የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ለተማሪዎቻቸው የሚቀርቡትን የምግብ ዝርዝር ባለፈው አመት ጀምሮ ተመሳሳይ ማድረጋቸው የሚታወስ ነው፡፡
የቴሌግራም ቻናላችን ይቀላቀሉ 👉 https://t.me/menaharia_fm
__
ሀሳብ እና’ሳ’ፍራለን 📞
👉011-639-28-52
👉011-639-37-63 (https://stream.zeno.fm/yw8poig9iwtuv)
ምላሽ ይስጡ