ሕዳር 04 ቀን 2018(መናኸሪያ ሬዲዮ)የካናዳ ተማሪ የሞባይል ስልክ ውስጥ የሚገኘውን ጥቃቅን የፍጥነት መለኪያ ‘ቺፕ’ በመጠቀም የመሬት መንቀጥቀጥን አስቀድሞ የሚጠቁም ሴንሰር የመፍጠር ሀሳብ ይዞ ብቅ ብሏል። ይህ ፈጠራ ውድ የሆኑ የሲስሚክ ጣቢያዎችን ሳይጠይቅ፣ ቀድሞውንም በሕዝብ እጅ ያሉ በሚሊዮን የሚቆጠሩ ስልኮችን በመጠቀም የቅድመ ማስጠንቀቂያ መረብ ለመገንባት የሚያስችለውን ዓለም አቀፍ ጥረት የሚያጠናክር ነው።
ዘመናዊ ስልኮች የቦታ አቀማመጥንና እንቅስቃሴን ለመለካት የሚያገለግል ‘አክሲሌሮሜትር’ የሚባል ሴንሰር አላቸው። ተማሪው የፈጠረው ሥርዓት የመሬት መንቀጥቀጥ በሚከሰትበት ወቅት የሚፈጠረውን ንዝረት ለመለየት የሚያስችል ሲሆን፣ ይህንንም ከሌሎች የዕለት ተዕለት እንቅስቃሴዎች የሚመጣ ንዝረት የመለየት ብቃት አለው።
የመሬት መንቀጥቀጥ የመጀመሪያው ሞገድ በዝግታ ቢጓዝም፣ ከጥፋት አድራሹ ሁለተኛው ሞገድ በፊት የስልኩ አውታረ መረብ ማስጠንቀቂያውን በከፍተኛ ፍጥነት (በብርሃን ፍጥነት) ማስተላለፍ ያስችላል ነው የተባለው። ይህም ሰዎች “መውደቅ፣ መሸፈን እና መያዝ” የሚባለውን የደህንነት እርምጃ ለመውሰድ ወሳኝ የሆኑ ሴኮንዶችን ይሰጣቸዋል።
ይህ አይነቱ ፈጠራ፣ ባህላዊ የመሬት መንቀጥቀጥ መከታተያ ጣቢያዎች ጥቂት ወይም የሌሏቸው ቦታዎች ላይ፣ ቀድሞውንም በሕዝብ እጅ ያሉ ዘመናዊ ስልኮችን ወደ ዘመናዊ የደህንነት መሣሪያነት በመቀየር የሕይወት አድን አገልግሎት መስጠት ያስችላል።
ፎቶ: በ AI የበለጸገ ምስል
የቴሌግራም ቻናላችን ይቀላቀሉ 👉 https://t.me/menaharia_fm
__
ሀሳብ እና’ሳ’ፍራለን 📞
👉011-639-28-52
👉011-639-37-63 (https://stream.zeno.fm/yw8poig9iwtuv)
ምላሽ ይስጡ