ጥቅምት 28 ቀን 2018(መናኸሪያ ሬዲዮ)ቻይና በባዮሚሜቲክስ ቴክኖሎጂ ዘርፍ አዲስ ምዕራፍ የሚከፍት የባህር ውስጥ የክትትል ድሮን ይፋ ማድረጓ ተዘገበ። ‘የመናፍስት ጀሊፊሽ’ (Ghost Jellyfish) የሚል ስያሜ የተሰጠው ይህ ሮቦት፣ ልክ እንደ እውነተኛው ጀሊፊሽ ቅርፅ ያለው ሲሆን፣ ለድብቅ እና ጸጥተኛ የውሃ ውስጥ ክትትል ታስቦ የተሰራ ነው ተብሏል።
በቻይና ሳይንቲስቶች የተሰራው ይህ የላቀ ድሮን፣ በውሃ ውስጥ ሲንቀሳቀስ በሶናር ወይም በዓይን ለመለየት እጅግ አስቸጋሪ በሆነ መልኩ የተቀየሰ ነው። ሮቦቱ የተሰራው በዋናነት ግልፅ ከሆነ የሃይድሮጀል ቁስ ሲሆን፣ የጀሊፊሽን ጡንቻ እንቅስቃሴ የሚመስል ጸጥተኛ የሆነ አክትዩዌተር ይጠቀማል።
በትንሹ የኃይል ፍጆታ ለረጅም ጊዜ በውኃ ውስጥ መቆየት የሚችል ሲሆን፣ ለሥነ-ምህዳር ጥናት፣ የባህር ውስጥ መሠረተ-ልማት ቁጥጥር፣ እና ለውሃ ውስጥ የስለላ ተልዕኮዎች ልዩ ብልጫ እንደሚሰጥ የፕሮጀክቱ መሪዎች ገልፀዋል።
በተጨማሪም ይህ ድሮን በካሜራ ሞጁል እና በአርቴፊሻል ኢንተለጀንስ ቺፕ የተገጠመለት በመሆኑ፣ የውሃ ውስጥ ነገሮችን ለይቶ የማወቅና የመከታተል ብቃት አለው።
ይህ የቻይና ፈጠራ፣ በውሃ ውስጥ የሚደረጉ የስለላ እና የምርምር ሥራዎችን ወደ አዲስ ደረጃ እንደሚያሸጋግር የዘርፉ ተንታኞች ይናገራሉ።
የቴሌግራም ቻናላችን ይቀላቀሉ 👉 https://t.me/menaharia_fm
__
ሀሳብ እና’ሳ’ፍራለን 📞
👉011-639-28-52
👉011-639-37-63 (https://stream.zeno.fm/yw8poig9iwtuv)
ምላሽ ይስጡ