ጥቅምት 27 ቀን 2018(መናኸሪያ ሬዲዮ)አንድ የጃፓን ባል ከባለቤቱ ጋር ከረጅም ጊዜ በፊት ከተፈጠረ አለመግባባት በኋላ ለሙሉ ሃያ ዓመታት ያህል መናገር ማቆሙ ተዘገበ። ይህ አስደናቂ የቤተሰብ ታሪክ የጃፓንን ማኅበረሰብ አስገርሟል።
የቶኪዮ ግዛት ነዋሪ የሆኑት ኦቶ ካታያማ የተባሉት ባል፣ ከባለቤታቸው ዩሚ ጋር ንግግር ማቆም የጀመሩት ከሁለት አስርት ዓመታት በፊት ነው። እንደተዘገበው ከሆነ፣ የአቶ ኦቶ የዝምታ ምክንያት ሚስታቸው ሙሉ ትኩረቷን ለልጆቻቸው እንክብካቤ በመስጠቷ ምክንያት ቅናት (jealousy) ተሰምቷቸው ነበር። ይህም መጀመሪያ ላይ በኩርፊያ የጀመረው ምላሽ ወደ ረዥም የዝምታ መቆም አድጓል።
ባለቤታቸው ዩሚ በበኩላቸው፣ ባላቸው ለጥያቄዎቿ ሁሉ ምላሽ መስጠት ያቆመ ቢሆንም፣ እርሷ ግን በተለመደው ሁኔታ ለሱ ማውራቷን እና ጥያቄዎችን መጠየቋን እንዳልተወች ተናግረዋል።
አባታቸው ከእናታቸው ጋር መናገር ካቆሙ በኋላ የተወለደው ልጃቸው፣ ይህን የቤተሰብ ሁኔታ በቴሌቪዥን ፕሮግራም ላይ የእርዳታ ጥሪ በማቅረብ ታሪኩን ለሕዝብ ይፋ አድርጓል።
በዚህ መርሃግብር አማካኝነት በተሰጠው ድጋፍ፣ ባልና ሚስቱ በፓርክ ውስጥ ተገናኝተው ለመነጋገር ተስማምተዋል። አቶ ኦቶ በመጨረሻ ዝምታቸውን ሰብረው ለባለቤታቸው ጥቂት ቃላትን ከተናገሩ በኋላ፣ ሁለቱ ጥንዶች በመጨረሻ ከ20 ዓመታት በኋላ ለመግባባት እና ትዳራቸውን ለመቀጠል ወስነዋል።
ወደ ቴሌግራም ይምጡ 👉 https://t.me/menaharia_fm
__
ሀሳብ እና’ሳ’ፍራለን 📞
👉011-639-28-52
👉011-639-37-63 (https://stream.zeno.fm/yw8poig9iwtuv)
ምላሽ ይስጡ