👉ወንጀለኛው በፖሊስ እየተፈለገ ፖሊስ የለጠፈውን ፎቶ ሲመለከት “ፎቶዬ አያምርም” ብሎ ሌላ የሰልፊ ፎቶ አንስቶ ለፖሊስ በመላኩ በቁጥጥር ስር ውሏል ነው የተባለው።
ጥቅምት 27 ቀን 2018(መናኸሪያ ሬዲዮ)በአሜሪካ ኦሃዮ ግዛት በህግ ሲፈለግ የነበረ አንድ ተከሳሽ፣ ፖሊስ ለዜና ማሰራጫዎች የላከው ፎቶግራፍ ስላልተመቸው፣ ተሻሽሎ የተነሳውን ‘ሴልፊ’ በማንሳት ለፖሊስ መምሪያ መላኩን የኦሃዮ ፖሊስ አስታወቀ።
የ45 ዓመቱ ዶናልድ ፑቺ በተለያዩ ወንጀሎች ተፈላጊ ሆኖ ሲፈለግ የነበረ ሲሆን፣ ፖሊስ ማንነቱን ለሕዝብ ለማሳወቅ የድሮ የእስር ቤት ፎቶውን በቴሌቪዥንና በማህበራዊ ሚዲያ ለቋል።
ፑቺ የራሱን ፎቶ በዜና ላይ ሲመለከት “በጣም አስቀያሚ” ሆኖ ስላገኘው ተቆጥቶ ነበር። ወዲያውኑ ጥቁር መነፅር አድርጎ፣ ከመኪናው ውስጥ እያለ አማላይ ‘ሴልፊ’ በማንሳት ለፖሊስ ዲፓርትመንቱ የማህበራዊ ሚዲያ ገጽ ላከ።
ፖሊስ የፑቺን ድፍረትና የማህበራዊ ሚዲያ አጠቃቀም ተገንዝቦ፣ ፎቶውን በመለጠፍ “ስላሳሰብከን እናመሰግናለን፣ አዲሱ ፎቶህ የተሻለ ነው። አሁን ግን እባክህ ራስህን አሳልፈህ ስጥ” የሚል አስገራሚ አስተያየት ሰጥቷል።
ይህን አስገራሚ ክስተት ተከትሎ ፖሊስ በፑቺ አድራሻ ላይ ፍለጋውን አጠናክሮ በመቀጠል፣ ከጥቂት ቀናት በኋላ በፍሎሪዳ ግዛት ውስጥ በቁጥጥር ስር ለማዋል መቻሉን አክሎ ገልጿል።
የቴሌግራም ቻናላችን ይቀላቀሉ 👉 https://t.me/menaharia_fm
__
ሀሳብ እና’ሳ’ፍራለን 📞
👉011-639-28-52
👉011-639-37-63 (https://stream.zeno.fm/yw8poig9iwtuv)
ምላሽ ይስጡ