ጥቅምት 27 ቀን 2018(መናኸሪያ ሬዲዮ)ፈረንሳይ በከተማ አካባቢ ለስላሳ ነፋስን ወደ ንፁህ ኃይል በመለወጥ ረገድ አዲስ ምዕራፍ የከፈተችውን ፈጠራ ይፋ አደረገች።
የነፋስ ዛፍ በመባል የሚታወቀው ይህ አብዮታዊ ቴክኖሎጂ፣ በፈረንሳይ የሚገኘው ኒውዊንድ (Newwind) በተባለ ኩባንያ የተገነባ ነው። የከተማዋን ውበት ሳይነካ ለነፋስ ኃይል ማመንጫ የሚውሉ ባህላዊ ተርባይኖች ሊጠቀሙበት የማይችሉትን ለስላሳ የነፋስ ፍሰት ለመጠቀም ታስቦ የተሰራ ነው።
እያንዳንዱ “የነፋስ ዛፍ” እስከ 10 ኪሎዋት (kW) የሚደርስ ንጹህ ኃይል የማመንጨት አቅም አለው። መዋቅሩ ኃይልን የሚያመነጨው በቅርንጫፎቹ ላይ በተገጠሙ 36 አነስተኛ፣ የቅጠል ቅርጽ ባላቸው ተርባይኖች ነው። እነዚህ ትናንሽ ተርባይኖች ጸጥ ብለው የሚሰሩና በዝግታ በሚነፍስ ነፋስ በቀላሉ መንቀሳቀስ የሚችሉ ናቸው ተብሏል።
ይህ የፈረንሳይ ፈጠራ በከተሞች ውስጥ ታዳሽ ኃይልን ለማመንጨት አዲስና ውጤታማ አማራጭ እንደሚሆን ተስፋ ተጥሎበታል።
ወደ ቴሌግራም ይምጡ 👉 https://t.me/menaharia_fm
__
ሀሳብ እና’ሳ’ፍራለን 📞
👉011-639-28-52
👉011-639-37-63 (https://stream.zeno.fm/yw8poig9iwtuv)
ምላሽ ይስጡ