ጥቅምት 21 ቀን 2018(መናኸሪያ ሬዲዮ) ግብፅ በኢራን እና በዓለም አቀፉ የኒውክሌር ኃይል ኤጀንሲ (IAEA) መካከል በኢራን የኒውክሌር መርሃ ግብር ዙሪያ ትብብር እንዲኖር በዲፕሎማሲያዊ መንገድ ሽምግልና ማድረጓን ማጠናከሯን አስታወቀች።
የግብፅ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ባድር አብደላትቲ ከኢራን ምክትል የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አባስ አራግቺ እና ከIAEA ዋና ዳይሬክተር ራፋኤል ግሮሲ ጋር በስልክ ተነጋግረዋል። ንግግሩ የኢራንን የኒውክሌር ጉዳይ በሰላማዊ መንገድ ለመፍታት እና በክልሉ ያለውን ውጥረት ለመቀነስ ላይ ያተኮረ እንደነበር ተገልጿል።
ይህ ጥረት የመጣው ቀደም ሲል በግብፅ ሽምግልና መስከረም 9 ላይ በካይሮ የተፈረመውን እና ከሰኔ ወር ጀምሮ ታግዶ የነበረውን ትብብር ወደነበረበት የመመለስ ስምምነትን ተከትሎ ነው። ሚኒስትር አብደላትቲ በዚያ ማዕቀፍ መሰረት ትብብሩን ማስቀጠል እና ማስፋት አስፈላጊ መሆኑን አሳስበዋል።
የግብፅ ፕሬዚዳንት አብዱልፈታህ አል-ሲሲ በመካከለኛው ምስራቅ ውጥረትን የማርገብ ጥረቶች እንዲቀጥሉ በሰጡት መመሪያ መሠረት ይህ ዲፕሎማሲያዊ እንቅስቃሴ እንደቀጠለ ነው ተብሏል። ግብፅ በክልሉ የሰላምና የጸጥታ አየር ለመፍጠር የሚያስችል ገንቢ ውይይት እንዲኖር ለማመቻቸት ያለማቋረጥ እየጣረች እንደምትገኝ የካይሮ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር አስታውቋል።
የቴሌግራም ቻናላችን ይቀላቀሉ 👉 https://t.me/menaharia_fm
__
ሀሳብ እና’ሳ’ፍራለን 📞
👉011-639-28-52
👉011-639-37-63
(https://stream.zeno.fm/yw8poig9iwtuv)
የቀጥታ ስርጭት 🔊 👉  https://zeno.fm/radio/menahria-99-1-3pw1/ (https://stream.zeno.fm/yw8poig9iwtuv)


 
	 
											 
			 
			 
			 
			 
			 
			 
			 
			 
			 
			
ምላሽ ይስጡ