ጥቅምት 21 ቀን 2018(መናኸሪያ ሬዲዮ) ጃፓን ሰው ሰራሽ ጥርሶችን (Dentures) እና የጥርስ ተከላዎችን (Implants) ወደ ታሪክ የሚሰድ አዲስ ዘመን ሊከፍት የሚችል አብዮታዊ መድኃኒት በሰዎች ላይ መሞከር መጀመሯን አስታወቀች። ይህ ግኝት የተፈጥሮ ጥርስን በሰውነት ውስጥ እንደገና ማብቀል የሚቻልበትን መንገድ ያመላክታል።
የጃፓን ተመራማሪዎች፣ በተለይም በኪዮቶ ዩኒቨርሲቲ የሚገኙ ሳይንቲስቶች፣ USAG-1 የተሰኘውን ፕሮቲን የሚገታ መድኃኒት አዘጋጅተዋል። ይህ ፕሮቲን በተፈጥሮ የሰው ልጅ ሦስተኛ ዙር ጥርስ እንዳያበቅል የሚከላከል “ብሬክ” እንደሆነ ይታመናል።
አዲሱ መድኃኒት (TRG-035) ይህን ብሬክ በማስወገድ፣ በሰውነት ውስጥ ያሉትን የተኙ የጥርስ “ቡቃያዎች” እንዲነቃቁ እና አዲስ፣ ተፈጥሯዊ ጥርስ እንዲያበቅሉ ያስችላል ተብሎ ይጠበቃል።
የመድኃኒቱ የመጀመሪያ ምዕራፍ ሙከራ የተጀመረው በአዋቂ በጎ ፈቃደኞች ላይ ሲሆን፣ ዋና ዓላማው የመድኃኒቱን ደኅንነት ማረጋገጥ ነው። በአይጦችና ፈረሶች ላይ በተደረጉ ቀደምት ሙከራዎች መድኃኒቱ ስኬታማ ውጤት አስመዝግቧል ነው የተባለው።
ሙከራው በተሳካ ሁኔታ ከቀጠለ፣ መድኃኒቱ ጥርስ በማጣት ለሚሰቃዩ ሕፃናትና ለአረጋውያን መፍትሔ ይሰጣል ተብሎ ይጠበቃል። ሳይንቲስቶች መድኃኒቱ በ2030 ገበያ ላይ እንዲውል ለማድረግ አቅደዋል።
ይህ ግኝት በዓለማቀፍ የጥርስ ሕክምና ታሪክ ትልቅ ለውጥ የሚያመጣና ሰዎች የተፈጥሮ ጥርሳቸውን መልሰው እንዲያገኙ ተስፋ የሚሰጥ አዲስ ምዕራፍ ነው።
የቴሌግራም ቻናላችን ይቀላቀሉ 👉 https://t.me/menaharia_fm
__
ሀሳብ እና’ሳ’ፍራለን 📞
👉011-639-28-52
👉011-639-37-63
(https://stream.zeno.fm/yw8poig9iwtuv)
የቀጥታ ስርጭት 🔊 👉  https://zeno.fm/radio/menahria-99-1-3pw1/ (https://stream.zeno.fm/yw8poig9iwtuv)


 
	 
											 
			 
			 
			 
			 
			 
			 
			
ምላሽ ይስጡ