👉ተቋሙ አሁንም ድረስ ፖወሮችን እና የኤሌትሪክ ምሶሶችኖን ወይም ፖሎችን በኪራይ መልክም እየተጠቀመ እንደሚገኝም አስታውቋል።
ጥቅምት 20 ቀን 2018(መናኸሪያ ሬዲዮ) ይህንን ያለው ባለፉት ሶስት አመታት በስራ ላይ ቆይታውን እያደረገ የሚገኘው ሳፋሪኮም ኢትዮጵያ የተሰኘው ተቋም ነው።
ተቋሙ ከመገናኛ ብዙሀን ከተውጣጡ ሙያተኞች ጋር ገለፃ እያደረገ የሚገኝ ሲሆን በቆይታውም ከምስረታው አንስቶ አሁን ያለበትን ደረጃንም እያብራራ ይገኛል።
የተቋሙ የውጭ ግንኙነት ሀላፊ ዶክተር አንዱለም አድማሴ እንዳሉት ተቋማቸው በርካታ ሼሮች እና ሰራተኞችን በመያዝ ስራዎችን እያከናወነ እንደሚገኝም ነው የጠቆሙት።
በዚህም በመንግሥት በኩል በየዓመቱ ከሚሰበሰበው የግብር መጠን ከፍተኛውን እየከፈለ እንደሚገኝ የተገለፀ ሲሆን በዚህም ባለፉት ሶስት አመታት ብቻ 12 ቢሊየን የሚሆነውን የግብር መጠን ለመንግሥት መክፈል ስለመቻሉም ነው የገለፁት ።
አክለውም ተቋማቸው በቀን ውስጥ 40ሺህ የሚሆኑ አዳዲስ ደንበኞችን እንደሚያገኝ እና በወር ውስጥ 1 ሚሊየን የሚሆኑ አዳዲስ ደንበኞች እንዲሁም በአመት ውስጥም 2.5 ሚሊየን የሚሆኑ ደንበኞችን ያገኛል ሲሉም አብራርተዋል ።
አያይዘውም በአሁኑ ሰዓት ኢትዮጵያ በአፍሪካ ደረጃ በሁለተኛነት የህዝብ ብዛት ያለባት ሀገር ብትሆንም ካላት መልከአምድር አንፃር 35 በመቶ ያህል ብቻ በሚሆነው የሀገሪቱ ክፍል ላይ ዜጎች እየኖሩ እንደሚገኙ ገልፀው ፤ቀሪው ቁጥር ምንም አይነት ስራዎች ያልተከናወኑባቸው ከመሆናቸው ባለፈም ዜጎች ኑሯቸውን እያደረጉባቸው አይደለም ብለዋል።በዚህም ተቋሙ በቀጣይ የሚሰራቸው ስራዎችን እንዳሉም ጠቅሰዋል ።
አያይዘውም ሀገሪቱን በቴሌኮም ዘርፉ ላይ እድገት ማሳየት እንድትችልም የመሰረተ ልማት ስራዎች ላይ በተገቢው መንገድ መስራት ላይ ማሟላት ተገቢ ስለመሆኑ ይጠቁማሉ።
ሆኖም በአሁኑ ሰዓት ኢትዮጵያ ከያዘችው የህዝብ ቁጥር አንፃር ያላት የታወር መጠን ከ11 እስከ 13 መሆኑን ገልፀው፤ከሌሎች ሀገራት ተሞክሮ አንፃር ተጨማሪ ስራዎች ማከናወን እንደሚጠበቅባት የሌሎች ሀገራትን ተሞክሮ በማንሳትም ያብራራሉ።
ይሁን እንጂ አሁንም በሀገሪቱ የፖወር ተከላ ላይ የሚታዩ ተግዳሮቶች መኖራቸውን አንስተው ፤በዚህ ላይም መስራት ይፈልጋል ብለዋል።
ተቋሙ በቆይታው 3,200 ታወር በጠቅላላው እንዳለው የገለፀ ሲሆን በሀገሪቱ ተጨማሪ 25 ሺህ ታወር የሚያስፈልግ እንደሆነ ጠቁመው የሚያስወጣው ወጪም 5 ቢሊዮን ዶላር እንደሆነም ገልጿል ።
የቴሌግራም ቻናላችን ይቀላቀሉ 👉 https://t.me/menaharia_fm
__
ሀሳብ እና’ሳ’ፍራለን 📞
👉011-639-28-52
👉011-639-37-63
(https://stream.zeno.fm/yw8poig9iwtuv)
የቀጥታ ስርጭት 🔊 👉 https://zeno.fm/radio/menahria-99-1-3pw1/ (https://stream.zeno.fm/yw8poig9iwtuv)
ምላሽ ይስጡ