ጥቅምት 20 ቀን 2018(መናኸሪያ ሬዲዮ) ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ ኢትዮጵያ የባህር በር ያጣችበትን ስምምነትና የውሳኔ ሰነድ ማገኘት እንዳልተቻለ እና ሀገሪቷ ባህር በሯን ያጣችበት መንገድ ህጋዊ አካሄዶችን ያልተከተለ መሆኑን ገልጸዋል፡፡ በወቅቱ የነበሩ የካብኔ እና የምክር ቤት አባላት ያልተወያዩበት፤ ውሳኔም ያላሳለፉበት እንደሆነ ለምክር ቤት አባላት አስታውቀዋል፡፡
መናኸሪያ ሬዲዮም ያነጋገራቸው የምክር ቤት አባልና የዓለም አቀፍ ህግ ባለሙያ መረጃው ይፋ መደረጉ በቀጣይ ሀገሪቷ በሠላማዊ መንገድ የባህር ባሯን ለማስመልስ ለምታደረገው ጥረት አጋዥ ነው ብለዋል፡፡
በተለያዩ ሀገራት በአምባሳደርነት አገራቸውን ያለገሉት አምባሳደር የሺመብራት መርሻ፤ በቀጣይ ልምድ ያላቸው ዲፕሎማት፤ ዓለም አቀፍ የህግ ባለሙያዎችና የዘርፉን ምሁራን በማሰባሰብ ስትራቴጂካዊ እቅድ ማዘጋጀት እንደሚገባው ገልጸዋል፡፡
ዓለም አቀፍ የህግ ባለሙያው አቶ ጥጋቡ ደሳለኝ በበኩላቸው በ1985 ዓ.ም በሽግግር ወቅት ኢትዮጵያ ሁለት ወደቦቿን ያጣችበት መንግድ አግባብነት የጎደለው መሆኑን ገልጸው፤ ቢያንስ ከሁለት ወደቦች አንዱን መውሰድ ይገባት ነበር ብለዋል፡፡
በ1987 ዓ/ም በወጣው እና አሁንም ተግባራዊ እየተደረገ ባለው የኢትዮጵያ ህገ መንግስት አንቀፅ 72 ንዑስ 2 ስር የጠቅላይ ሚንስትሩ፤ የሚንስትሮች ምክር ቤት እና የካብኔ አባላት የጋራ ውሳኔ የሀገሪቷ ውሳኔ ተደርጎ እንደሚወሰድ በማመላከት፤ በ1985 የተወሰነው ውሳኔ ግን ሀገሪቷ የሽግግር መንግስት ላይ ሁና ብሄራዊ ጥቅሟን የሚነካ ዘላቂ ወሳኔዎች መተላለፋቸው ቅቡልነት የሌለው መሆኑን አስረድተዋል፡፡
አሁን ላይ ኢትዮጵያ እነዚህን ማስረጃዎች በመያዝ ወደ ዓለም አቀፍ ገላጋይ ፍርድ ቤቶች ማምራትና ማሳወቅ ይጠበቅባታል ብለዋል፡፡
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ ኢትዮጵያ ያጣችሁን ወደብ መልሳ ለማገኘት ያጣችሁን ያህል ጊዜ እንደማይወስድባት መናገራቸው ይታወሳል፡፡
የቴሌግራም ቻናላችን ይቀላቀሉ 👉 https://t.me/menaharia_fm
__
ሀሳብ እና’ሳ’ፍራለን 📞
👉011-639-28-52
👉011-639-37-63
(https://stream.zeno.fm/yw8poig9iwtuv)
የቀጥታ ስርጭት 🔊 👉 https://zeno.fm/radio/menahria-99-1-3pw1/ (https://stream.zeno.fm/yw8poig9iwtuv)
ምላሽ ይስጡ