ጥቅምት 17 ቀን 2018(መናኸሪያ ሬዲዮ)የኢትዮጵያ ሃገራዊ ምክክር ኮሚሽን ለታጠቁ ሃይሎች በተደጋጋሚ ጥሪ ቢያቀርብም አብዛኛዎቹ ጥሪውን እንዳልተቀበሉ ኮሚሽኑ በተደጋጋሚ ሲገልፅ መቆየቱ የሚታወስ ነው፡፡
የኮሚሽኑ የስራ ዘመን እስኪገባደድ ድረስ አሁንም የታጠቁ ሃይሎች የኮሚሽኑን ጥሪ ተቀብለው አጀንዳቸውን እንዲያስረክቡ የጠየቁት የኮሚሽኑ ኮሚሽነር ዶክተር ዮናስ አዳዬ፤ ኮሚሽኑ በመንግስት በኩል ሙሉ ዋስትናን ማቅረብ እንደሚችል ተናግረዋል፡፡
የታጠቁ ሃይሎች አጀንዳቸውን ሊያስረክቡ ሲቀርቡ እስከ ትጥቃቸው መቅረብ እንደሚችሉ የገለፁት ኮሚሽነሩ፤ በምክክሩ ለሚሳተፉት የታጠቁ አካላት ኮሚሽኑ ተገቢውን የጥበቃ ዋስትና እንደሚያመቻችና ከኢትዮጵያም ውጪ በፈለጉት ቦታ ውይይት ለማድረግ ፍቃደኛ መሆኑን ገልፀዋል፡፡
በኮሚሽኑ በኩል የተፈጠረውን እድል ሁሉም የማህብረተሰብ ክፍሎች ሊጠቀሙበት እንደሚገባም አንስተው፤ ኮሚሽኑ የስራ ዘመን ቆይታው ሊጠናቀቅ የቀረው ጊዜ አጭር ቢሆንም አሁንም ከታጣቂዎች ጋር በተደጋጋሚ ውይይት ለማድረግ አጀንዳ ለመሰብሰብ እየሞከረ መሆኑን ተናግረዋል፡፡
የታጠቁ ሃይሎች የመንግስትን የሰላም ጥሪ በመቀበል ወደ ሰላም እንዲመጡ ኮሚሽነር ዶክተር ዮናስ አዳዬ በድጋሚ ጥሪ አቅርበዋል፡፡
አሁን ላይ በኢትዮጵያ በተለያዩ አከባቢዎች ያለው ግጭት እና የሰላም እጦት በወንድማማቾች መካከል የሚካኤድ ነው ብለው እንደሚያምኑ የገለጹት ኮሚሽነሩ የታጠቁ ሃይሎች አጃንዳቸውን በተወካዮች ሲልኩ እስከ ትጥቃቸው መላክ እንደሚችሉ አስታውቀዋል፡፡
የቴሌግራም ቻናላችን ይቀላቀሉ 👉 https://t.me/menaharia_fm
__
ሀሳብ እና’ሳ’ፍራለን 📞
👉011-639-28-52
👉011-639-37-63
(https://stream.zeno.fm/yw8poig9iwtuv)
የቀጥታ ስርጭት 🔊 👉 https://zeno.fm/radio/menahria-99-1-3pw1/ (https://stream.zeno.fm/yw8poig9iwtuv)
ምላሽ ይስጡ