ጥቅምት 17 ቀን 2018(መናኸሪያ ሬዲዮ) ይህ የተገለፀው የቅዱስ ሲኖዶስ ምልዓተ ጉባዔ መጠናቀቁን ተከትሎ በተሰጠው ጋዜጣዊ መግለጫ ላይ ነው፡፡
የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ቅዱስ ሲኖዶስ ምልዓተ ጉባዔ ከጥቅምት 11 እስከ 17 ቀን 2018 ዓ.ም ያካሄደውን ውይይት በዛሬዉ እለት አጠናቋል።
የቤተክርስቲያኒቷን አንድነት ለማስጠበቅ ለትውልድ እንዲተላለፍ ሁሉም ምእመን ሀላፊነቱን ሊወጣ እንደሚገባ በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን ቅዱስ ሲኖዶስ ዋና ፀሀፊ እና የራያ ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ ብፁዓ አቡነ ዲዮስቆሮስ ተናግረዋል፡፡
ቅዱስ ሲኖዶስ በትግራይ ሀገረ ስብከት መካከል የተፈጠረውን የመዋቅር ግንኙነቱን ወደ ቀድሞው እንዲመለስ ነው ጥሪ ያቀረበው፡፡ ከዚህ በተጨማሪም የሲኖዶሱ ምዕላተ ጉባኤ ዉሳኔ ካሳለፈባቸዉ ጉዳዮች መካከል በቤተክርስቲያቱ በዓላት ወቅት የሚታዩ ክፍተቶችን ለማረም ለአገልጋዮች የማስተማሪያ ሰነድ እንዲዘጋጅ ወሳኔ ማሳለፍም ይገኝበታል፡፡ ፡፡
በሰሜን ሸዋ ሀገረ ስብከት በምንጃር ሸንኮራ ወረዳ በአረርቲ ደብረ ገነት ቅድስት ማርያም ቤተ ክርስቲያን በደረሰው አደጋ ጉዳት ለደረሰባቸው ወገኖች ለማሳከምና የተጎጂ ቤተሰቦችን ለመርዳት የገንዘብ ድጋፍ እንዲደረግም ቅዱስ ሲኖዶስ መወሰኑንም አቡነ ዲዮስቆርስ ገልጸዋል፡፡ በቅድስት ቤተክርስቲያኒቷ የሚገነቡ ግንባታዎች ከፍተኛ ጥንቃቄ ሊደረግባቸው እንደሚገባም ቅዱስ ሲኖዶስ አሳስቧል፡፡ በመላው ሀገሪቱ የሚገኙ አካላት ወደ ሰላም እንዲመጡም ጥሪ ቀርቧል፡፡
ቅዱስ ሲኖዶሱ በቤተ ክርስቲያኒቱ መንሳፈዊ አስተዳደርና ማኅበራዊ ጉዳዮችን መሠረት ባደረጉ አጀንዳዎች ላይ ለ7 ቀናት ውይይት አካሂዶ ውሳኔዎች ማሳለፉን አስታውቋል።
የቴሌግራም ቻናላችን ይቀላቀሉ 👉 https://t.me/menaharia_fm
__
ሀሳብ እና’ሳ’ፍራለን 📞
👉011-639-28-52
👉011-639-37-63
(https://stream.zeno.fm/yw8poig9iwtuv)
የቀጥታ ስርጭት 🔊 👉 https://zeno.fm/radio/menahria-99-1-3pw1/ (https://stream.zeno.fm/yw8poig9iwtuv)
ምላሽ ይስጡ