ጥቅምት 17 ቀን 2018(መናኸሪያ ሬዲዮ) በተያዘው በጀት ዓመት በሶስት ወራት ውስጥ ትክከለኛ የመንገድ አጠቃቀም ያልተከተሉ 11ሺህ508 እግረኞች በገንዘብ እና በማህበራዊ አገልግሎቶች አንዲሰጡ ማድረግ እንደተቻለም ነው ባለስልጣን መስሪያ ቤቱ ያስታወቀው፡፡
በባለሥልጣን መ/ቤቱ እንዳለውም በአስራ አንዱም ቅርንጫፍ ጽ/ቤቶች በኩል በሩብ ዓመቱ በተካሄደ ጥብቅ ቁጥጥር የመንገድ ትራንስፖርትን ለመቆጣጠር በወጣው በደንብ ቁጥር 557/2016 መሰረት በትክክለኛው የእግረኛ መሻገሪያ መንገድን ያላቋረጡ፤ በተሽከርካሪ መንገድ ላይ ያለ በቂ ምከንያት የቆሙ ወይም የተጓዙ እንዲሁም የእገረኛ መንገድ በሌለበት ቀኝ ጠርዛቸውን ይዘው የተጓዙ እግረኞች ከግንዛቤ ማስጨበጥ ባለፈ ከብር 100 እስከ 1መቶ50 ብር አንዲቀጡ ስለማድረጉም አስታውቋል፡፡
እንዲሁም የጆሮ ማዳመጫ በማድረግ መንገድን ያቋረጡ፣ ለእግረኛ ተብለው የተከለሉ አጥሮችን የዘለሉና ለሎችንም የመንገድ ትራፊክ ደንብ የተላለፉ 11 ሺህ 508 እግረኞች የእርምት እርምጃ እንደተወሰደባቸውም ነው ያስታወቀው፡፡
ደንቡን ከተላለፉ እግረኞች መካከል 6ሺህ108ቱን በገንዘብ፤ 5ሺህ499ኙን እግረኞች ደግሞ የከተማ ጽዳት፣ አቅመ ደካሞቸን ማገዝ እና ሌሎቸንም ማህበራዊ አገልግሎቶቶ አንዲሰጡ መደረጉን ያስታወቀው ባለስልጣን መስሪያ ቤቱ ነው፡፡
የእገረኛ ቁጥጥር ተጠናክሮ በቀጣይም የከተማዋን የትራፊክ ፍስት ሰላማዊ ለማድረግና የመንገድ ተጠቃሚውን ሀብረተሰብ ከተሸከርካሪ አደጋ ለመጠበቅ ሲባል የሚሰሩ ስራዎች ተከታታይነት እንዳላቸው እና የሚቀጥሉ ስለመሆኑም አስታውቋል፡፡
የቴሌግራም ቻናላችን ይቀላቀሉ 👉 https://t.me/menaharia_fm
__
ሀሳብ እና’ሳ’ፍራለን 📞
👉011-639-28-52
👉011-639-37-63
(https://stream.zeno.fm/yw8poig9iwtuv)
የቀጥታ ስርጭት 🔊 👉 https://zeno.fm/radio/menahria-99-1-3pw1/ (https://stream.zeno.fm/yw8poig9iwtuv)
ምላሽ ይስጡ