ጥቅምት 15 ቀን 2018(መናኸሪያ ሬዲዮ)የሩሲያው ፕሬዝዳንት ቭላድሚር ፑቲን ልዩ መልዕክተኛ እንደተናገሩት፣ ሩሲያ፣ አሜሪካ እና ዩክሬን አብረው በመስራት በዩክሬን እየተካሄደ ያለውን ጦርነት በዲፕሎማሲያዊ መፍትሔ ለመቋጨት ተቃርበዋል ብለዋል፡፡
መልዕክተኛው የሰጡት መግለጫ የሚያመለክተው፣ በሁለቱ ኃያላን መንግስታት (ሩሲያ እና አሜሪካ) መካከል ተከታታይ ውይይቶች መደረጋቸውን ተከትሎ፣ ለሰላም የሚበጅ የጋራ መግባባት ለመፍጠር ተስፋ ሰጪ ዕድል መፈጠሩን ነው።
የፑቲን መልዕክተኛው ቃል፣ ከቀናት በፊት በዋሽንግተን እና ሞስኮ ከፍተኛ ዲፕሎማቶች መካከል በሰላም ንግግር ዙሪያ መሻሻሎች ታይተዋል ከሚለው ዘገባ ጋር የሚጣጣም ነው። በጦርነቱ ላይ ያሉ ተጋጭ ወገኖች (ሩሲያ እና ዩክሬን) እንዲሁም ዋነኛው ደጋፊ (አሜሪካ) ወደ የጋራ መግባባት መቃረባቸውን ነው ያመለከቱት።
ይሁን እንጂ፣ ዩክሬን የሩሲያን ወረራ ሙሉ በሙሉ በማውገዝ እና የወሰደችውን ግዛት ማስመለስ በሚያስችል ሁኔታ ብቻ ስምምነት ላይ መድረስ እንደሚቻል አቋሟን አጥብቃ እንደያዘች ትገኛለች። በመሆኑም፣ የዲፕሎማሲያዊው መፍትሔ ዝርዝር ይዘት እና ሁሉም ወገኖች የሚያደርጉት ስምምነት ምን እንደሚመስል እስካሁን በይፋ አልተገለጸም።
በተባበሩት መንግስታት ድርጅት (ተመድ) እና በሌሎች ዓለም አቀፍ አካላት በኩል ጦርነቱ እንዲቆም የሚደረገው ጥረት ተጠናክሮ በቀጠለበት በዚህ ወቅት፣ ከሩሲያ በኩል የወጣው ይህ አስተያየት የዓለም አቀፉ ማኅበረሰብ በጉጉት የሚጠበቀውን የሰላም ዕድል የሚያጎላ ነው።
የቴሌግራም ቻናላችን ይቀላቀሉ 👉 https://t.me/menaharia_fm
__
ሀሳብ እና’ሳ’ፍራለን 📞
👉011-639-28-52
👉011-639-37-63
(https://stream.zeno.fm/yw8poig9iwtuv)
የቀጥታ ስርጭት 🔊 👉 https://zeno.fm/radio/menahria-99-1-3pw1/ (https://stream.zeno.fm/yw8poig9iwtuv)
ምላሽ ይስጡ