ጥቅምት 11 ቀን 2018(መናኸሪያ ሬዲዮ) ብዙ ጊዜ እንደ አላስፈላጊ ነገር ከግድግዳ ላይ የምናስወግደው ሞስ (Moss)፣ ዝም ብሎ የዕፅዋት ማስጌጫ ብቻ ሳይሆን፣ የተደበቀ የአየር ንብረት ጀግና መሆኑ ተረጋግጧል።
ይህ ጥቃቅን ተክል፣ በአየር ንብረት ለውጥ እና በከተማ ሙቀት ላይ የሚያበረክተው አስተዋጽኦ እጅግ አስገራሚ ነው ተብሏል። ሞስ፣ በአንድ ካሬ ሜትር የገጽታ ስፋት ከዛፎች በአራት እጥፍ ብልጫ ያለው ኮርቦን ዳይ ኦክሳይድ የመያዝ አቅም እንዳለው የሳይንስ ጥናቶች ያመለክታሉ።
ይህ አቅሙ በተጨናነቁ ከተሞች ውስጥ ቦታን በአግባቡ ለመጠቀም ያስችላል። በተጨማሪም ሞስ ከፍተኛ መጠን ያለው ውሃ የመያዝ ችሎታ ስላለው፣ በከተሞች ውስጥ ያለውን ሙቀት በመቀነስ እና እርጥበትን በመጠበቅ የተፈጥሮ የአየር ማቀዝቀዣ አገልግሎት ይሰጣል ነው የተባለው። ይህ የሞስ ባህሪ በተለይ የከተማ ሙቀት ደሴት ተብሎ የሚጠራውን ችግር ለመቀነስ ወሳኝ እንደሆነም ተመላክቷል፡፡
ከሙቀት በተጨማሪ ሞስ በአየር ውስጥ የሚገኙ ጎጂ የሆኑ መርዛማ ንጥረ ነገሮችን እና ጥቃቅን የአቧራ ቅንጣቶችን በመያዝ፣ በከተማ አካባቢ ያለውን የአየር ንጽህና በእጅጉ ያሻሽላል ተብሏል። የሞስ ሌላው ጠቀሜታ መሬት አለመፈለጉ ነው የተባለ ሲሆን ግድግዳዎች፣ ጣራዎችና በኮንክሪት ላይ በቀላሉ ይበቅላል። ይህ ደግሞ በከተማ ልማት ውስጥ አረንጓዴ ቦታዎችን ለመፍጠር ትልቅ እድል ይፈጥራል ነው የተባለው። ሞስ ውሃ፣ ማዳበሪያ ወይም ልዩ እንክብካቤ ሳይፈልግ ይለመልማል፤ እንዲሁም የአፈር መሸርሸርን ይከላከላል እና እርጥበትን ይዞ ይቆያል ነው የተባለው።
ይህ ሁሉ ታላቅ ጥቅም ቢኖረውም፣ አብዛኛው የከተማ ነዋሪዎች ሞስን እንደ አላስፈላጊ ነገር በማየት ያጠፉታል። ባለሙያዎች እንደሚናገሩት፣ የዓለማችንን እጅግ ውጤታማ የአየር ንብረት አጋር ማጥፋት ቆም ብለን የምናስብበት ተግባር ሲሆን፣ ሞስን ማስወገድ አቁመን በእሱ መገንባት መጀመር ለከተማችን ዘላቂ መፍትሔ እንደሚያመጣ ተመላክቷል፡፡
የቴሌግራም ቻናላችን ይቀላቀሉ 👉 https://t.me/menaharia_fm
__
ሀሳብ እና’ሳ’ፍራለን 📞
👉011-639-28-52
👉011-639-37-63
(https://stream.zeno.fm/yw8poig9iwtuv)
የቀጥታ ስርጭት 🔊 👉 https://zeno.fm/radio/menahria-99-1-3pw1/ (https://stream.zeno.fm/yw8poig9iwtuv)
ምላሽ ይስጡ