ጥቅምት 11 ቀን 2018(መናኸሪያ ሬዲዮ) የኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዴሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ጽህፈት ቤት፣ የተለያዩ ቋሚ ኮሚቴዎች ለነገ ረቡዕ ጥቅምት 12 ቀን 2018 ዓ.ም ያዘጋጇቸውን የሥራ መርሐግብሮች አስታውቋል።
የፍትሕ ሚኒስቴር ዕቅድ ግምገማ
የሕግና ፍትሕ ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ፣ የፍትሕ ሚኒስቴር የ2018 በጀት ዓመት ዕቅድ እና የ1ኛው ሩብ ዓመት ዕቅድ አፈጻጸም ሪፖርትን በዝርዝር ለመገምገም ፕሮግራም ይዟል። ግምገማው ነገ ረቡዕ ጥቅምት 12 ቀን 2018 ዓ.ም ከጠዋቱ 2፡30 ጀምሮ በምክር ቤቱ የመሰብሰቢያ አዳራሽ እንደሚካሄድ ተገልጿል።
በግብርና ረቂቅ አዋጆች ላይ ውይይት
በተመሳሳይ የግብርና ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ በአንድ ቀን ውስጥ ሁለት የተለያዩ መርሐግብሮችን አዘጋጅቷል።
1.የሕዝብ ይፋዊ ውይይት፡ ኮሚቴው በባለብዙ ተዋንያን የግብርና ኤክስቴንሽን አገልግሎትና አስተዳደር ረቂቅ አዋጅ ላይ የሕዝብ ይፋዊ ውይይት ለማካሄድ ረቡዕ ጥቅምት 12 ቀን 2018 ዓ.ም ከጠዋቱ 2፡30 ጀምሮ በምክር ቤቱ የመሰብሰቢያ አዳራሽ ቀጠሮ ይዟል።
2.የአስረጅዎች መድረክ፡ ከሰዓት በኋላ ደግሞ፣ የዕፅዋት ጥበቃ እና ከኳራንቲን ረቂቅ አዋጅ ላይ ከሚመለከታቸው ሚኒስቴር መስሪያ ቤቶች ጋር የአስረጅዎች መድረክ ለማካሄድ መርሐግብር ተይዟል። ይህ መድረክ ረቡዕ ጥቅምት 12 ቀን 2018 ዓ.ም ከቀኑ 7፡30 ጀምሮ በምክር ቤቱ የመሰብሰቢያ አዳራሽ ይካሄዳል።
እነዚህ የቋሚ ኮሚቴዎች መርሐግብሮች የመንግሥት የሥራ አፈጻጸምን ለመቆጣጠር እና በሀገሪቱ አስፈላጊ በሆኑ ረቂቅ አዋጆች ላይ ግልጽ ውይይት በማድረግ ሕጉ ከመጽደቁ በፊት የባለድርሻ አካላትን አስተያየት ለማሰባሰብ ያለመ መሆኑን መረጃው ያመለክታል።
የቴሌግራም ቻናላችን ይቀላቀሉ 👉 https://t.me/menaharia_fm
__
ሀሳብ እና’ሳ’ፍራለን 📞
👉011-639-28-52
👉011-639-37-63
(https://stream.zeno.fm/yw8poig9iwtuv)
የቀጥታ ስርጭት 🔊 👉 https://zeno.fm/radio/menahria-99-1-3pw1/ (https://stream.zeno.fm/yw8poig9iwtuv)
ምላሽ ይስጡ