ጥቅምት 11 ቀን 2018(መናኸሪያ ሬዲዮ) ባለፈው ሚያዚያ 2023 በአገሪቱ የጦር ኃይል እና በፈጥኖ ደራሽ ሃይሉ መካከል ጦርነት ከተቀሰቀሰበት ጊዜ በኋላ ለመጀመሪያ ጊዜ የካርቱም አውሮፕላን ማረፊያ ለሀገር ውስጥ በረራ ክፍት እንደሚደረግ ተገልጿል።
የሱዳን ሲቪል አቪዬሽን ባለስልጣን በሀገሪቱ በቀጠለው ግጭት ምክንያት ለ30 ወራት ተዘግቶ የቆየው የካርቱም አለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ ከነገ ረቡዕ ጀምሮ ለአገር ውስጥ በረራ ክፍት እንደሚሆን አስታውቋል።
ውሳኔው የአየር ማረፊያው የቴክኒክ እና የኦፕሬሽን ዝግጅቶችን ካጠናቀቀ በኋላ ቀስ በቀስ በረራዎችን እያስፋፋ ለመሄድ ያለውን ዝግጁነት ያረጋግጣል ሲል ኤጀንሲው አክሎ ገልጿል።
በገሪቱ የጦር ሠራዊት እና ፈጥኖ ደራሽ ሃይሉ መካከል በተፈጠረው ጦርነት የካርቱም ዓለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ ከሁለት ዓመት ተኩል በላይ ለሚሆን ጊዜ ሥራውን አቁሞ እንደነበር ይታወቃል።
ከሚያዝያ 2023 ጀምሮ በነበረው ጦርነቱ ከ20ሺሕ በላይ ሰዎች መሞታቸው እና 14 ሚሊዮን የሚሆኑት መፈናቀላቸውን የተባበሩት መንግስታት ድርጅት እና የአካባቢው ባለስልጣናት መረጃ አመላክቷል።
በአሜሪካ ዩኒቨርሲቲዎች የተደረጉ ጥናቶች ግን የሟቾችን ቁጥር ወደ 130ሺ ከፍ ያደርጋሉ።
የጦር ሃይሉ ከሚያዚያ 2023 ወዲህ ለመጀመሪያ ጊዜ ባለፈው መጋቢት 27፣ አየር ማረፊያውን፣ በርካታ የደህንነት እና ወታደራዊ ተቋማትን እንዲሁም ከዋና ከተማው ምስራቅ እና ደቡብ ያሉ ሰፈሮችን ከተቆጣጠረ በኋላ በካርቱም ግዛት ያለው የፈጥኖ ደራሽ ኃይሉን ምሽጎች እንዳወደመ ዘገባው አስታውሷል።
ከነገ ጀምሮ ደግሞ ለ30 ወራት ተዘግቶ የቆየው የካርቱም አውሮፕላን ማረፊያ ለአገር ውስጥ በረራ ክፍት ይደረጋል ተብሏል ያለው የአናዶሉ ዘገባ ነው።
የቴሌግራም ቻናላችን ይቀላቀሉ 👉 https://t.me/menaharia_fm
__
ሀሳብ እና’ሳ’ፍራለን 📞
👉011-639-28-52
👉011-639-37-63
(https://stream.zeno.fm/yw8poig9iwtuv)
የቀጥታ ስርጭት 🔊 👉 https://zeno.fm/radio/menahria-99-1-3pw1/ (https://stream.zeno.fm/yw8poig9iwtuv)
ምላሽ ይስጡ