ጥቅምት 10 ቀን 2018(መናኸሪያ ሬዲዮ)የኢትዮጵያ መገናኛ ብዙሃን ባለሙያዎች ማህበር ከቀናት በፊት 4ተኛ ጠቅላላ ጉባዔውን አከናውኗል።
መናኸሪያ ሬዲዮ ያነጋገራቸው የማህበሩ ፕሬዝዳንት ወይዘሮ እታግ መኮንን፤ ማህበሩ ተቀማጭነቱ አዲስ አበባ ቢሆንም በክልል ደረጃም የአባላቱን ቁጥር ለማሳደግ እየሰራ እንደሚገኝ አስታውቀዋል።
በአሁኑ ሰዓት ከ260 በላይ የሚሆኑ አባላቱን ይዞ የተለያዩ ስራዎችን እያከናወነ እንደሚገኝ ተናግረዋል።
ከዚህ ቀደም በማህበሩ ስር በርካታ ቁጥር ያላቸው አባላት የነበሩ ቢሆንም፤ አብዛኞቹ የማህበሩ አላማ ያልገባቸው፤ ከሙያው የራቁ እንዲሁም ለአላማው መሳካት የሚጠበቅባቸውን አበርክቶ የማይወጡ በመሆኑ አባላቱ እንደ አዲስ መዋቀራቸውን አስታውቀዋል፡፡
ማህበሩ በአሁኑ ሰዓት ጠንካራ ስራዎችን እየሰራ እንዳለ የሚገልጹት ፕሬዝዳንቷ፤ ነገር ግን ባለፉት ጊዜያት ገጥመውት በነበሩ ችግሮች ምክንያት ተቀዛቅዞ እንደቆየ ተናግረዋል።
ወቅቱን ጠብቆ ሪፖርት ባለመቅረቡ ማስጠንቀቂያ እንደተሰጣቸው፤ በእዳ ምክንያትም ቢሮው የተዘጋበት ሁኔታ እንደነበር አስታውቀዋል።
ማህበሩን በዋነኝነት ሲመሩ የነበሩ ሙያተኞችም ወደ ውጪ መውጣታቸው ሌላኛው ፈተና እንደሆነ ጠቁመዋል።
በቀጣይ ማህበሩን በማጠናከር ለሙያው እና ሙያተኞች መብት መከበር እንደሚሰራ አስታውቀዋል፡፡
የቴሌግራም ቻናላችን ይቀላቀሉ 👉 https://t.me/menaharia_fm
__
ሀሳብ እና’ሳ’ፍራለን 📞
👉011-639-28-52
👉011-639-37-63
(https://stream.zeno.fm/yw8poig9iwtuv)
የቀጥታ ስርጭት 🔊 👉 https://zeno.fm/radio/menahria-99-1-3pw1/ (https://stream.zeno.fm/yw8poig9iwtuv)
ምላሽ ይስጡ