ጥቅምት 10 ቀን 2018(መናኸሪያ ሬዲዮ)የውሃና ኢነርጂ ሚኒስቴር የንጹህ መጠጥ ውሃአቅርቦትን በሁሉም የሀገሪቱ ክፍል ተደራሽ ለማድረግ በጥናት የታገዘ የቁፋሮ ስራ እንደሚሰራ በሚንስቴሩ የንጹህ መጠጥ ውሃና ሳኒቴሽን ዘርፍ የመጠጥ ውሃ ተቋማት ክትትል ዴስክ ሃላፊ አቶ ሃይማኖት በለጠ ተናግረዋል፡፡
ከዚህ ቀደም በየአከባቢው የከርሰ ምድር ውሃ መጠንን በማጥናት እና በመቆፈር ለማህበረሰቡ የንጹህ መጠጥ ውሃ ተደራሽ ይደረግ እንደነበር ገልጸው፤ አሁን ላይ በተለያዩ አካባቢዎች ዘላቂ ተብለው የተቆፈሩ የከርሰ ምድር ውሃ እየደረቁ መሆኑን በጥናት ማረጋገጥ ተችሏል ብለዋል፡፡
በሃገራችን በስፋት በሰሜኑ ክፍል እና በአዲስ አበባ አቃቂ የከርሰ ምድር ውሃን ለመቆፈር ባለሙያዎች ጥናት ሲያደርጉ ከግምታዊ ጥናቱ በታች እየሆነ እንዳለም አቶ ሐይማኖት አስታውቀዋል፡፡
የከርሰ ምድር ውሃ ከፍተኛ ወጪ የሚጠይቅ ቢሆንም በየአከባቢው ለማዳረስ አመቺ እንደሆነ የገለጹት አቶ ሐይማኖት፤ ዘላቂ ምንጭ የሚሆነው ግን የገጸ ምድር ውሃ መሆኑን አመላክተዋል፡፡
በጥናቱ መሰረት ለከርሰ ምድር ውሃ መቀነስ ቀዳሚው ምክንያት የአካባቢ መራቆት እንደሆነ ገልጸዋል፡፡ ሚኒስቴሩ ዘላቂ የውሃ ተደራሽነትን ለማረጋገጥ አስቸጋሪ ቢሆንም ጥናቶችን በማድረግ የገፀ ምድር ውሃን ለመጠቀም እንደሚሰራ አስታውቀዋል፡፡
የተለያዩ ማሽኖችን በመጠቀም የከርሰ ምድር ውሃን አውጥቶ ለማህበረሰቡ ተደራሽ ማድረግ እንደሚቻል ሚናገሩት ኃላፊው፤ የገፀ ምድር ውሃ ግን ሃይቆችና ወንዞች በቅርብ ርቀት ከሌሉ ተደራሽ ለማድረግ እንደሚያስቸግር አመላክተዋል፡፡
የቴሌግራም ቻናላችን ይቀላቀሉ 👉 https://t.me/menaharia_fm
__
ሀሳብ እና’ሳ’ፍራለን 📞
👉011-639-28-52
👉011-639-37-63
(https://stream.zeno.fm/yw8poig9iwtuv)
የቀጥታ ስርጭት 🔊 👉 https://zeno.fm/radio/menahria-99-1-3pw1/ (https://stream.zeno.fm/yw8poig9iwtuv)
ምላሽ ይስጡ