ጥቅምት 06 ቀን 2018(መናኸሪያ ሬዲዮ)በ2017 ዓ.ም 52.3 ቢሊዮን ብር ዋጋ ያላቸውን የህክምና ግብአቶች ግዢ መፈጸሙን የኢትዮጵያ መድሀኒት አቅራቢ አገልግሎት ለጣቢያችን አስታውቋል።
ግዢውም በመደበኛ በጀትና በእርዳታ ገንዘብ መፈጸሙን ያሳወቀው ተቋሙ በተጨማሪውም በተገኘ ፈንድና በጤና ፕሮግራም የህክምና ግብአቶች በ64.5 ቢሊየን ብር ግዢ በመፈጸም ለጤና ተቋማት መሰራጨቱን ገልጸዋል።
የክህምና ግብዓቶቹን ከውጭ ሀገራት ከማስመጣት ባሻገር 4.6 ቢሊዮን ብር የሚያወጡ ግብአቶችን ከሀገር ውስጥ አምራቾች መረከብ መቻሉን ተገልጿል።
ባሳለፍነው አመት የጸጥታ እና የወረርሽኝ ችግር ባሉባቸው አካባቢዎች የህክምና ግብአቶችን ማድረስ መቻሉ ተጠቁሟል።
ካሁን ቀደም የነበሩ የዱቤ የሽያጭ ሁኔታን ማሻሻል መቻሉን በማንሳት ከ4 ሺህ 970 ጤና ተቋማት ውስጥ 4 ሺህ 910 ተቋማት የራሳቸው በጀት ይዘው ውል መግባታቸውን ተመላክቱል።
የቴሌግራም ቻናላችን ይቀላቀሉ 👉 https://t.me/menaharia_fm
__
ሀሳብ እና’ሳ’ፍራለን 📞
👉011-639-28-52
👉011-639-37-63
(https://stream.zeno.fm/yw8poig9iwtuv)
የቀጥታ ስርጭት 🔊 👉 https://zeno.fm/radio/menahria-99-1-3pw1/ (https://stream.zeno.fm/yw8poig9iwtuv)
ምላሽ ይስጡ