ጥቅምት 06 ቀን 2018(መናኸሪያ ሬዲዮ)ከመስከረም እስከ ታህሳስ ያለው ወቅት የወባ ትንኝ የሚፈለፈልበት መሆኑን ተከትሎ በተቀናጀ ሁኔታ በየሳምንቱ በየክልሎች ያለውን ፤የመገምገም ስራ እየተሰራ መሆኑን የኢትዮጵያ ህብረተሰብ ጤና ኢኒስቲትዩት ዋና ዳይሬክተር ዶ/ር መሳይ ሃይሉ ለመናኸሪያ ሬዲዮ አስታውቀዋል፡፡
ካለፈው አመት ተመሳሳይ ወቅት አንጻር የወባ ስርጭቱ መሻሻል የታየበት እንደሆነና በየሳምቱም በስረጭቱ ዙሪያ በሚደረጉ ቅኝቶች ለዉጥ መኖሩን የሚጠቅሱት ዶ/ር መሳይ ካለፈው ሳምንት ከነበረው ስርጭት አንጻር አሁን ላይ በ4 ነጥብ 4በመቶ እንደ ሃገር መቀነሱን ተናግረዋል።
አሁን ላይ እየታየ ያለው የወባ ስርጭትና የመራባት መጠንን በመመልከት መዘናጋት እንዳይኖር ቀድሞ ለመከላለል የትንኝ ቁጥጥር ሰራዎች በስፋት እየተሰሩ መሆኑን ገልጸዋል።
በተጨማሪም የታመሙ ሰዎችን ለይቶ በቶሎ የማከምና መድሃኒት የጀመሩትን ተከታትሎ እንዲጨርሱ የማድረግ ስራዎች እየተሰሩ መሆኑንም ጠቁመዋል፡፡
የአጎበር ስርጭት በኢኒስቲትዩቱ መደበኛ የመከላከል ስራ በመሆኑ በክልሎች በስፋት የማሰራጨት ሰራ መሰራቱን ገልጸው ከአጠቃቀም አንጻር የግንዛቤ ማስጨበጫ ሰራዎች መሰራታቸውን አመላክተዋል።
የክትትልና የቁጥጥር ስራው በክልሎች እንዳለው የተጋላጭነት ሁኔታ በብሄራዊ ግብረሃይሎች አማካኝነት በስፋት እየትሰራ መሆኑን አብራርተዋል።
የቴሌግራም ቻናላችን ይቀላቀሉ 👉 https://t.me/menaharia_fm
__
ሀሳብ እና’ሳ’ፍራለን 📞
👉011-639-28-52
👉011-639-37-63
(https://stream.zeno.fm/yw8poig9iwtuv)
የቀጥታ ስርጭት 🔊 👉 https://zeno.fm/radio/menahria-99-1-3pw1/ (https://stream.zeno.fm/yw8poig9iwtuv)
ምላሽ ይስጡ