ጥቅምት 06 ቀን 2018(መናኸሪያ ሬዲዮ)የአዲስ አበባ ከተማ ሰላምና ፀጥታ አስተዳደር ቢሮ ከአዲስ አበባ ከተማ ደንብ ማስከበር ባለስልጣን ጋር የ2018 ዓ.ም 1ኛ ሩብ ዓመት የስራ አፈጻጸምን ከማዕከል እስከ ወረዳ ካሉ ጽ/ቤት ኃላፊዎች አስተባባሪዎችና ቡድን መሪዎች ጋር በከንቲባ ጽ/ቤት እያከናወነ ይገኛል።
የመድረኩን የመክፈቻ ንግግር ያደረጉት የአዲስ አበባ ሰላም እና ፀጥታ ቢሮ ሀላፊ ወይዘሮ ሊዲያ ግርማ እንዳሉት በመዲናዋ ትላልቅ ይዘት ያላቸው ጉባዔዎች መከናወናቸው አስታውሰው፤እነዚሁ ጉባዔዎች በሰላም እንዲጠናቀቁ የፀጥታ አካላት የሰሩት ስራ የሚበረታታ ነዉ ብለዋል።
አክለውም በሩብ ዓመቱ መልካም የሚባሉ አፈፃፀሞች የታዩበት እንደሆና በዚህም ደግሞ በቢሮው በኩል በዘለቄታነት የተደረጉ ሪፎርሞች የራሳቸውን የሆነ ሚና እንዳላቸዉም አስረድተዋል፡፡
አያይዘውም ለሚሰሩ ስራዎች እንቅፋትን የሚፈጥሩ እና ተግዳሮት የሆኑ ጉዳዮችን በመለየት የህግ-ማዕቀፎችን የማዘጋጀት ስራም የተሰራበት ሁኔታ እንዳለም ጠቅሰዋል።
መዲናዋ ሰላሟ እና ደህንነቷ እንዲጠበቅ በማድረግ ውስጥ የማህበረሰቡ ሚናም ከፍተኛ ነዉ ብለዉ፤ ዜጎችን የሰላም ባለቤት ወይንም አካል ማድረግ አስፈላጊ በመሆኑ በሩብ አመቱ 11 ሺህ የሚሆኑ ምልምል ሰራዊትን ቢሮ አሰልጥኖ ወደ ስራ ማስገባት እንደቻለም ጠቁመዋል፡፡
አክለውም የሚፈፀሙ ወንጀሎችን በ43 በመቶ መቀነስ የተቻለበት ሁኔታ እንዳለ አስረድተው፤ከዚሁ ጋር በተገናኘም የቁማር ቤቶች ላይም በተመሳሳይ እርምጃ መወሰዱን ተናግረዋል፡፡
የመዲናዋን የሰላም ሁኔታ አስመልክቶ በደንብና በስርዓት እየተመራች ትገኛለች ብለው፤በመዲናዋ የሚከናወነውን የመሬት ወረራን አስመልክቶም ህግ እና ስርዓት እንዲበጅለት እየተሰራበት እንዳለ በዚህ ዓመትም በተመሳሳይ እንደሚቀጥል ጠቁመዋል፡፡
የቴሌግራም ቻናላችን ይቀላቀሉ 👉 https://t.me/menaharia_fm
__
ሀሳብ እና’ሳ’ፍራለን 📞
👉011-639-28-52
👉011-639-37-63
(https://stream.zeno.fm/yw8poig9iwtuv)
የቀጥታ ስርጭት 🔊 👉 https://zeno.fm/radio/menahria-99-1-3pw1/ (https://stream.zeno.fm/yw8poig9iwtuv)
ምላሽ ይስጡ