ጥቅምት 05 ቀን 2018(መናኸሪያ ሬዲዮ) ችግሩን ለመፍታትም ባለፈው አመት በመገጭ ወንዝ ላይ የግንባታ ስራ የተጀመረ ቢሆንም እስካሁን ግን የመጣ መፍትሄ እንደሌለ ተመላክቷል፡፡
በ20 ቀን አንድ ጊዜ አነሰ ሲባልም በ15 ቀን አንድ ጊዜ ብቻ ንጹህ የመጠጥ ውሃ እንደማያገኙ ለጣቢያችን የተናገሩት የጎንደር ከተማ የንጹህ መጠጥ ውሃ አቅርቦት የስራ ሂደትና ምክትል ስራ አስኪያጅ አቶ መኳንት ቢራራ ናቸው፡፡ በከተማው በኩል ችግሩ እንዳይባባስ ከዚህ ቀደም ተቆፍረው የተቀመጡ ጉድጓዶች ላይ የተለያዩ ስራዎችን በመስራት ተደራሽ እያደረጉ እንደሆነ ገልጸዋል፡፡
ችግሩን በዘላቂነት ለመፍታት በውሃና ኢነርጅ ሚኒስቴር በኩል በአካባቢው ጉድጓድ ለመቆፈርና ከጎንደር ከተማ በቅርብ እርቀት የሚገኘውን የመገጭ ግድብን ለመጠቀም የተጀመረ ስራ ቢኖርም ችግሩን መፍታት እንዳልተቻለ አቶ መኳንት ተናግረዋል፡፡
የጎንደር ከተማ የንጹህ መጠጥ ውሃ ችግርን በዘላቂነት ለመፍታት የመገጭ ወንዝ ግድብ እንዲሁም ከጣና ሃይቅ ወደ ከተማው የመሳብ ስራ ተጀምሮ እንደነበር ያመላከቱት በውሃና ኢነርጅ ሚንስቴር የንጹህ የመጠጥ ውሃና ሳኒቴሽን ዘርፍ የመጠጥ ውሃ ተቋማት ክትትል ዴስክ ሃላፊ አቶ ሃይማኖት በለጠ ስራው በተፈለገው ጊዜ እንዳይጠናቀቅ ከፍተኛ የሆነ የበጀት ችግር ፈተና ሆኗል ብለዋል፡፡
የመገጭንም ሆነ የጣናን ውሃ ጠልፎ ለመጠቀም ከ4 ቢሊዮን ብር በላይ ያስፈልጋል ብለው ችግሩን ለመፍታት ሲባል በመገጭና በጣና ላይ ባለሙያዎቹ ጥናት እንዳደረጉና ዘላቂ መፍትሔ እንደሚያስፈልገውም ገልጸዋል፡፡
የጣና ሃይቅን ስቦ ከመጠቀምና የመገጭ ግድብን በተመለከተ ግን በቂ የሆነ በጀት በማፈላለግ ላይ እንደሆኑና የሚጠናቀቅበት ጊዜም በጀቱ እስካልተገኘ ድረስ እንደማይታወቅ ተናግረዋል፡፡
በጎንደር ከተማ የንጹህ መጠጥ ውሃ እጥረት ካጋጠመ አመታት መቆጠራቸው ይታወቃል፡፡
የቴሌግራም ቻናላችን ይቀላቀሉ 👉 https://t.me/menaharia_fm
__
ሀሳብ እና’ሳ’ፍራለን 📞
👉011-639-28-52
👉011-639-37-63
(https://stream.zeno.fm/yw8poig9iwtuv)
የቀጥታ ስርጭት 🔊 👉 https://zeno.fm/radio/menahria-99-1-3pw1/ (https://stream.zeno.fm/yw8poig9iwtuv)
ምላሽ ይስጡ