ጥቅምት 05 ቀን 2018(መናኸሪያ ሬዲዮ) የአሜሪካው ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ በንግድ ላይ ተጨማሪ ታሪፎችን ለመጣል ማሰባቸውን ተከትሎ ምላሽ በመስጠት፣ እንዲህ ያለው እርምጃ የአሜሪካን ኢኮኖሚም በእጅጉ እንደሚጎዳ አስጠንቅቃለች።
የስፔን መንግሥት ከፍተኛ ባለሥልጣናት እንደተናገሩት፣ በአንድ ወገን የሚጣሉ የንግድ ማዕቀቦች ዓለም አቀፍ ትብብርን ከማናጋት ባለፈ፣ ታሪፍ የሚጥለውንም አገር ህብረተሰብ እና ኩባንያዎች ዋጋ ያስከፍላል ተብሏል።
ትራምፕ በአንዳንድ የውጭ አገራት ላይ አዲስ የንግድ ታሪፎችን የመጣል ዕቅድ እንዳላቸው በቅርቡ ያሰሙ ሲሆን፣ ይህ ማስፈራሪያ በዋነኛነት በአውሮፓ ኅብረት እና በተወሰኑ አገራት ላይ ያነጣጠረ ነው ተብሏል።
የስፔን ባለሥልጣናት፣ የአውሮፓ ኅብረት በጋራ ሆኖ ከአሜሪካ ጋር ለንግድ ውይይት ዝግጁ መሆኑን አሳውቀዋል። ይሁን እንጂ፣ በአሜሪካ በኩል ያልተገባ የታሪፍ እርምጃ ከተወሰደ፣ የአውሮፓ ኅብረት አስፈላጊውን የመልሶ ማጥቂያ እርምጃ ለመውሰድ ዝግጅት እያደረገ መሆኑን አሳስበዋል።
የስፔን ኢኮኖሚ ባለሙያዎች እንዳመለከቱት፣ የአሜሪካ ሸማቾች በውጭ ምርቶች ላይ በሚጣለው ታሪፍ ምክንያት ከፍተኛ ዋጋ እንዲከፍሉ ይገደዳሉ፤ ይህም በአሜሪካ ውስጥ የዋጋ ግሽበት እንዲጨምር ያደርጋል። በመሆኑም፣ የስፔን ምላሽ የንግድ ጦርነት ለማንም እንደማይጠቅም እና የአሜሪካ የኢኮኖሚ ጥቅምም እንደሚጎዳ የሚያሳስብ ነው።
የቴሌግራም ቻናላችን ይቀላቀሉ 👉 https://t.me/menaharia_fm
__
ሀሳብ እና’ሳ’ፍራለን 📞
👉011-639-28-52
👉011-639-37-63
(https://stream.zeno.fm/yw8poig9iwtuv)
የቀጥታ ስርጭት 🔊 👉 https://zeno.fm/radio/menahria-99-1-3pw1/ (https://stream.zeno.fm/yw8poig9iwtuv)
ምላሽ ይስጡ