ጥቅምት 04 ቀን 2018(መናኸሪያ ሬዲዮ)የ29 ዓመቷ ኬንያዊት የቁሳቁስ መሐንዲስ ንዛምቢ ማቴ ከስድስት ዓመታት በፊት በአካባቢ ላይ የፕላስቲክ ብክለትን ለመዋጋት ባላት ከፍተኛ ፍላጎት ምክንያት በነዳጅ ኢንዱስትሪ ውስጥ ትሰራ የነበረችበትን ሥራ ትታለች።
በናይሮቢ ከተማ ባቋቋመችው “ጂንጌ ሜከርስ ሊሚትድ” (Gjenge Makers Ltd) በተሰኘው አዲስ ኩባንያ፣ የተጣሉ ፕላስቲኮችን ከአሸዋ ጋር በማዋሃድ ባለብዙ ቀለም እና ከኮንክሪት የበለጠ ጥንካሬ ያላቸው ንጣፍ መሥሪያ ጡቦችን (paving bricks) በማምረት ላይ ትገኛለች።
የዚህ ፈጠራ ውጤት ትልቅ ኢኮኖሚያዊና ማኅበራዊ ለውጥ እያስከተለ ነው። ዛሬ ጂንጌ ሜከርስ በየዕለቱ 1,500 ጡቦችን በማምረት ከ20 ቶን በላይ የሚሆን የፕላስቲክ ቆሻሻን መልሶ ጥቅም ላይ ማዋል ችሏል። ከዚህም በላይ ይህ ሥራ ለሴቶች፣ ለወጣቶች እና ለቆሻሻ ሰብሳቢዎች ከ100 በላይ የሥራ ዕድሎችን በመፍጠር የማኅበረሰቡን ኢኮኖሚ በማጠናከር ላይ ይገኛል።
የንዛምቢ ማቴ ፈጠራ በኬንያ የአካባቢ ጥበቃን ከኢኮኖሚ ልማት ጋር በማጣመር፣ ዘላቂነት ያለው ልማትን በአፍሪካ ለማስረፅ አንድ ሀሳብ ምን ያህል ከተማን እና ማኅበረሰብን እንደሚለውጥ በግልጽ ያሳያል።
የቴሌግራም ቻናላችን ይቀላቀሉ 👉 https://t.me/menaharia_fm
__
ሀሳብ እና’ሳ’ፍራለን 📞
👉011-639-28-52
👉011-639-37-63
(https://stream.zeno.fm/yw8poig9iwtuv)
የቀጥታ ስርጭት 🔊 👉 https://zeno.fm/radio/menahria-99-1-3pw1/ (https://stream.zeno.fm/yw8poig9iwtuv)
ምላሽ ይስጡ