መስከረም 29 ቀን 2018(መናኸሪያ ሬዲዮ)ደቡብ ኮሪያዊያን ተመራማሪዎች በዓለም ለመጀመሪያ ጊዜ ታላቅ የሕክምና ምዕራፍ አስመዝግበዋል። የጉሮሮ ካንሰር ቀዶ ሕክምና ወቅት የንፋስ ቧንቧዋ (ትራኪያዋ) የተጎዳባትን ሴት፣ በ3D-የታተመ ሰው ሰራሽ ትራኪያ በመተካት ተሳክቶላቸዋል።
ሰው ሰራሽ የንፋስ ቧንቧው የታተመው በታካሚዋ ገዛ ሕያው ሕዋሳት (እንደ የ cartilage እና የ mucosal ሕዋሳት) አማካኝነት ነው። እነዚህ ሕዋሳት አዲስ ሕብረ ሕዋስ በተፈጥሮው እንዲያድግ በሚያግዝ PCL (Polycaprolactone) ከተባለ ባዮዲግሬድድ (በጊዜ ሂደት የሚበሰብስ) ፖሊመር አጽም ጋር ተቀናጅተው በባዮ-ኢንክ (bio-inks) በመጠቀም ታትመዋል። አጽሙ ለመዋቅሩ መረጋጋት የሰጠ ሲሆን፣ የሰውነቷ ሕዋሳት በላዩ ላይ እንዲያድጉ አስችሏል።
ከተተከለ ከስድስት ወራት በኋላ ዶክተሮች በተተከለው ቧንቧ ዙሪያ አዳዲስ የደም ሥሮች መፈጠራቸውን ተመልክተዋል። ይህ የሚያሳየው ሰውነት ምንም ዓይነት የሰውነት መከላከያ አቅም የሚቀንሱ መድኃኒቶችን ሳይፈልግ ተከላውን መቀበሉንና ሕብረ ሕዋሱን በራሱ ማደስ መጀመሩን ነው።
ይህ ስኬት በሴኡል ሴንት ሜሪ ሆስፒታል (Seoul St. Mary’s Hospital) ከቲ ኤንድ አር ባዮፋብ (T&R Biofab) ጋር በመተባበር የተከናወነ ሲሆን፣ ለመልሶ ማደስ ሕክምና እና ለሕብረ ሕዋስ ምህንድስና ትልቅ ምዕራፍ ነው። ባለሙያዎች ይህ ስኬት ሳንባዎችን፣ ኩላሊቶችን አልፎ ተርፎም ልብን ከመሰሉ ውስብስብ የሰውነት ክፍሎች የታካሚውን ሕዋስ በመጠቀም 3D-ማተም ወደሚቻልበት ዘመን እጅግ አቅርቦናል ይላሉ።
የቴሌግራም ቻናላችን ይቀላቀሉ 👉 https://t.me/menaharia_fm
__
ሀሳብ እና’ሳ’ፍራለን 📞
👉011-639-28-52
👉011-639-37-63
(https://stream.zeno.fm/yw8poig9iwtuv)
የቀጥታ ስርጭት 🔊 👉 https://zeno.fm/radio/menahria-99-1-3pw1/ (https://stream.zeno.fm/yw8poig9iwtuv)
ምላሽ ይስጡ