መስከረም 26 ቀን 2018(መናኸሪያ ሬዲዮ)ይህ የተነገረው 6ኛው የኢፌዴሪ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤትና የፌዴሬሽን ምክር ቤት 5ኛ ዓመት የሥራ ዘመን መክፈቻ ሥነ ሥርዓት ላይ ነው፡፡
የኢፌድሪ ፕሬዝደንት ታዬ አጽቀስላሴ እንዳሉትም በ2018 ዓ.ም የመንገድ አውታር ስራዎችን ለማከናወን እየተሰሩ ያሉ ስራዎችን መኖራቸውን ጠቁመው፤በተለይ የአየር ትራንስፖርት፤የኤሌትሪክ እንዲሁም የታዳሽ ሀይላን ማሳደግ የምትችልበት ስራንም ለማከናወን እንደምትሰራ አንስተዋል፡፡
አክለውም በገጠሪቱ የሀገሪቱ ክፍል የንጹህ የመጠጥ ውሃ አቅርቦት ላይም ስራዎች እየተሰሩ ስለመሆኑ አስታውቀው፤በሀገሪቱ ያሉ የቱሪዝም መዳረሻ ስፍራዎቸ በኩልም የሚነሱ የመሰረተ -ልማት ጥያቄዎች ለማሟላት እና መዳረሻ ስፍራቹን ለነዋሪዎችም ሆነ ለጎብኚዎች ምቹ የማድረግ ስራ ይሰራልም ሲሉ አስታውቀዋል፡፡
የቴሌግራም ቻናላችን ይቀላቀሉ 👉 https://t.me/menaharia_fm
__
ሀሳብ እና’ሳ’ፍራለን 📞
👉011-639-28-52
👉011-639-37-63
(https://stream.zeno.fm/yw8poig9iwtuv)
የቀጥታ ስርጭት 🔊 👉 https://zeno.fm/radio/menahria-99-1-3pw1/ (https://stream.zeno.fm/yw8poig9iwtuv)
ምላሽ ይስጡ