መስከረም 22 ቀን 2018(መናኸሪያ ሬዲዮ)በአሜሪካ ውስጥ XFV (“ስትራተስ”) እና NB.1.8.1 (“ኒምበስ”) የሚባሉ ሁለት አዳዲስ የኮቪድ-19 ዝርያዎች በፍጥነት እየተሰራጩ ነው ተባለ። በተለይ በ ነቫዳ፣ ኮነቲከት፣ ዩታ እና ዴላዌር ግዛቶች የቫይረሱ ስርጭት በከፍተኛ ሁኔታ ጨምሯል።
ዶክተሮች እንደዘገቡት ከሆነ፣ አዲሶቹ ዝርያዎች ከተለመዱት የጉንፋን ምልክቶች (እንደ ድካም፣ ሳል እና ንፍጥ) በተጨማሪ ታማሚዎች ባልተለመደ ሁኔታ ከባድ የሆነ የጉሮሮ ህመም እየተሰማቸው ነው ብለዋል።
ታማሚዎቹ ይህን ህመም “ምላጭ እንደዋጥክ” ወይም “በጉሮሮ ውስጥ እንደተሰካ ምስማር” በማለት ይገልጹታል። ምንም እንኳን ባለሙያዎች እነዚህ ዝርያዎች ከቀደሙት ዝርያዎች የበለጠ ገዳይ አይመስሉም ብለው ቢያሳስቡም፣ አሁንም ቢሆን ለአረጋውያን፣ ለበሽታ የመከላከል አቅማቸው ደካማ ለሆኑ እና ለተለያዩ መሰረታዊ የጤና ችግሮች ላለባቸው ሰዎች አደጋ ይፈጥራሉ ተብሏል።
የጤና ስፔሻሊስቶች ቀላል የሚመስሉ የኮቪድ ጉዳዮች እንኳን ወደ ረጅም ኮቪድ ሊያመሩ እንደሚችሉ ያስጠነቅቃሉ። በአገር አቀፍ ደረጃ የኮቪድ ቫይረስ በቆሻሻ ውሃ ፍሳሽ ውስጥ ያለው መጠን የመቀነስ ምልክት ቢያሳይም፣ በአንዳንድ ክልሎች አሁንም የኢንፌክሽን መጠኑ “በጣም ከፍተኛ” ደረጃ ላይ እንደሚገኝ የሲዲሲ (CDC) የክትትል ሪፖርቶች ያመላክታሉ፡፡
የቴሌግራም ቻናላችን ይቀላቀሉ 👉 https://t.me/menaharia_fm
__
ሀሳብ እና’ሳ’ፍራለን 📞
👉011-639-28-52
👉011-639-37-63
(https://stream.zeno.fm/yw8poig9iwtuv)
የቀጥታ ስርጭት 🔊 👉 https://zeno.fm/radio/menahria-99-1-3pw1/ (https://stream.zeno.fm/yw8poig9iwtuv)
ምላሽ ይስጡ