መስከረም 21 ቀን 2018(መናኸሪያ ሬዲዮ)ፊሊፒንስን የመታውን ኃይለኛ የመሬት መንቀጥቀጥ ተከትሎ፣ የሟቾች ቁጥር ወደ 69 ከፍ ማለቱን የአገሪቱ ባለሥልጣናት አስታወቁ። የነፍስ አድን ሠራተኞች በፍርስራሽ ሥር የተገኙ ሰዎችን ለማትረፍ ከፍተኛ ጥረት እያደረጉ ነው።
የፊሊፒንስ የእሳተ ገሞራ እና የመሬት መንቀጥቀጥ ጥናት ተቋም ባወጣው መረጃ መሠረት፣ ረቡዕ ከሰዓት በኋላ እስከ 800 የሚጠጉ የመሬት መንቀጥቀጥ ድኅረ-ንቅናቄዎች (aftershocks) ተመዝግበዋል። እነዚህ ተደጋጋሚ ንቅናቄዎች የነፍስ አድን ሥራውን ይበልጥ አደገኛና ፈታኝ እያደረጉት ነው።
መሬት መንቀጥቀጡ በደረሰባቸው አካባቢዎች በርካታ ሕንፃዎች ፈርሰዋል፤ መንገዶችም ተጎድተዋል። የአካባቢው ባለሥልጣናት፣ ከባድ የመሬት መንሸራተትም አደጋውን እንዳባባሰው ገልፀዋል።
የመንግሥትና የዓለም አቀፍ የሰብዓዓዊ እርዳታ ድርጅቶች የምግብ፣ የውሃ እና የህክምና አቅርቦቶችን ለተጎጂዎች ለማድረስ በመንቀሳቀስ ላይ ናቸው። ፕሬዝዳንቱ በደረሰው ጥፋት ለተጎዱ ቤተሰቦች የተሰማቸውን ሐዘን በመግለጽ፣ መንግሥት ሁሉንም አስፈላጊ ድጋፎች እንደሚያደርግ ቃል ገብተዋል።
የቴሌግራም ቻናላችን ይቀላቀሉ 👉 https://t.me/menaharia_fm
__
ሀሳብ እና’ሳ’ፍራለን 📞
👉011-639-28-52
👉011-639-37-63
(https://stream.zeno.fm/yw8poig9iwtuv)
የቀጥታ ስርጭት 🔊 👉 https://zeno.fm/radio/menahria-99-1-3pw1/ (https://stream.zeno.fm/yw8poig9iwtuv)
ምላሽ ይስጡ