መስከረም 21 ቀን 2018(መናኸሪያ ሬዲዮ) በ2018 ዓ.ም በፍሎሪዳ በሚገኘው ማርጆሪ ስቶንማን ዳግላስ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት በተፈፀመው አሰቃቂ የተኩስ አደጋ ወቅት፣ የ15 ዓመቱ አንቶኒ ቦርጅስ ያሳየው ጀግንነት እስከዛሬ ድረስ የሚወሳ ሆኗል።
ቦርጅስ ተኳሹ ወደ ክፍል ውስጥ እንዳይገባ ለመከላከል ሰውነቱን ተጠቅሞ የክፍሉን በር በመጋረድ፣ ቢያንስ የ20 ተማሪዎችን ሕይወት ታድጓል።
በዚህ ጀግንነት በተሞላበት ተግባር ላይ ሳለ አምስት ጊዜ በጥይት የተመታው አንቶኒ ቦርጅስ፣ በርካታ ቀዶ ጥገናዎችን እና ረጅም የማገገም ጊዜን አሳልፏል። ድርጊቱ የአንድ ሰው መስዋዕትነት የብዙዎችን ሕይወት እንዴት እንደሚያድን የሚያሳይ የድፍረት እና ከራስ ወዳድነት የራቀ ተግባር ምልክት ሆኗል።
የአንቶኒ ቦርጅስ ጀግንነት በወቅቱ የአገሪቱን ቀልብ የሳበ ሲሆን፣ እያንዳንዱ ዜጋ ለሌሎች ደኅንነት የመቆም አቅም እንዳለው የሚያሳይ ሕያው ምሳሌ ሆኗል ነው የተባለው፡፡
የቴሌግራም ቻናላችን ይቀላቀሉ 👉 https://t.me/menaharia_fm
__
ሀሳብ እና’ሳ’ፍራለን 📞
👉011-639-28-52
👉011-639-37-63
(https://stream.zeno.fm/yw8poig9iwtuv)
የቀጥታ ስርጭት 🔊 👉 https://zeno.fm/radio/menahria-99-1-3pw1/ (https://stream.zeno.fm/yw8poig9iwtuv)
ምላሽ ይስጡ