መስከረም 21 ቀን 2018(መናኸሪያ ሬዲዮ)ካቢላ የኤም 23 አማፂ ቡድንን በመደገፍ በሀገሪቱ ምስራቃዊ ክልል ከፍተኛ ውድመት ያደረሰውን ወንጀል ፈጽመዋል ሲል የሃገሪቱ መንግስት ከሷቸዋል።
ካቢላ በሌሉበት በወታደራዊ ፍርድ ቤት በርካታ ክሶች የቀረቡባቸው ሲሆን እሳቸው ግን ክሱን ቀልድ ነው ብለውታል።
የቀድሞ ፕሬዝደንቱ በሃገር ክህደት፣ በንጹሃን ዜጎች ላይ በተፈፀመ ጥቃት፣ አማጽያንን በጦር መሣሪያ በመደገፍ፣ ዜጎችን በማሰቃየት፣ በጾታዊ ጥቃት እና በሌሎችም ወንጀሎች ጥፋተኛ ናቸው ሲል የሃገሪቱ ፍርድ ቤት የመጨረሻውን የሞት ፍርድ ውሳኔ አስተላልፏል።
የሃገሪቱ ፕሬዚደንት ፍሊክስ ትሺሴኪዲ- ጆሴፍ ካቢላ ከኤም 23 ጋር በመሆን ሃገራቸው እንዳትረጋጋ እንዳደረጉ ከከሰሱ በኋላ በህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ያለመከሰስ መብታቸው ተነስቶ የሞት ፍርድ ተበይኖባቸዋል።
የቀድሞው ፕሬዝደንት በስልጣን ላይ እያሉ የፈጸሙት ወንጀል አለመኖሩን በመግለጽ ካሉበት ሆነው ክሱን ውድቅ አድርገዋል።
ነገር ግን ራሳቸውን ለመከላከል ፍርድ ቤት መቅረብ አልቻሉም ሲል ቢቢሲ ዘግቧል።
የቴሌግራም ቻናላችን ይቀላቀሉ 👉 https://t.me/menaharia_fm
__
ሀሳብ እና’ሳ’ፍራለን 📞
👉011-639-28-52
👉011-639-37-63
(https://stream.zeno.fm/yw8poig9iwtuv)
የቀጥታ ስርጭት 🔊 👉 https://zeno.fm/radio/menahria-99-1-3pw1/ (https://stream.zeno.fm/yw8poig9iwtuv)
ምላሽ ይስጡ