👉1,255 ኪሎ ሜትር በዩኬ አቋርጦ እየተጓዘ ነው ተብሏል
መስከረም 21 ቀን 2018(መናኸሪያ ሬዲዮ) በዩናይትድ ኪንግደም ለንደን ከተማ የሚገኘው የኢምፔሪያል ኮሌጅ ተማሪ የሆነው ኢትዮጵያዊ የ24 ዓመቱ ወጣት ቅዱስ ተሰራ፣ ከሞላ ጎደል በድጋሚ ጥቅም ላይ ከዋሉ ዕቃዎች (Recycled Parts) እና ከእንጨት ብቻ በገዛ እጁ የሰራውን ብስክሌት በመጠቀም 780 ማይል(1,255 ኪሎ ሜትር) ርቀት በዩኬ ውስጥ በመጓዝ ላይ ይገኛል ተብሏል።
የባዮኬሚስትሪ ተማሪው ኪዱስ ይህን ልዩ ጉዞ የጀመረው፣ ብስክሌቱ በእርግጥም መሥራት እንደሚችልና አስተማማኝ መሆኑን ለማረጋገጥ ነው።
“ቅዱስ ተሰራ” ወደዚህ አስደናቂ ፈጠራ የመጣው፣ በሚያጠናበት ኢምፔሪያል ኮሌጅ የሥራ ቦታ (workshop) ላይ አንድ ያገለገለ ብስክሌት ጠግኖ ካጠናቀቀ በኋላ ነው። ይህ ሂደት በብስክሌት አሰራር ላይ በቂ እውቀት እንዳገኘ እንዲሰማው ያደረገ ሲሆን፣ በራሱ ልዩ ብስክሌት የመሥራት ሀሳብ እንዲመጣለት አነሳስቷል።
ወጣቱ ተማሪው በፈጠራው ላይ ሲሠራ፣ አሮጌ ብረቶችን፣ የተረፈ እንጨቶችን እና ከ9 ዓመቷ የአክስቱ ልጅ በዘጠኝ ፓውንድ የገዛውን የብስክሌት ክፍሎች ጭምር ተጠቅሟል።
አሁን እየተጓዘበት ያለው የእንጨት ፍሬም ያለው ብስክሌት፣ የጥንካሬውን እና የዘላቂነት መርህን በተግባር እያሳየ ሲሆን፣ ጉዞውን በመላው የዩናይትድ ኪንግደም ግዛት በመቀጠል ላይ ይገኛል።
ቅዱስ በጉዞው ለሚገጥሙት ደግ አስተናጋጆች ምስጋናን ለመግለጽ እና የዘላቂነትን መርህ ለማስተዋወቅ በማሰብ ለበጎ አድራጎት ድርጅቶች ገንዘብ የማሰባሰብ ሥራንም እያከናወነ ነው።
የቴሌግራም ቻናላችን ይቀላቀሉ 👉 https://t.me/menaharia_fm
__
ሀሳብ እና’ሳ’ፍራለን 📞
👉011-639-28-52
👉011-639-37-63
(https://stream.zeno.fm/yw8poig9iwtuv)
የቀጥታ ስርጭት 🔊 👉 https://zeno.fm/radio/menahria-99-1-3pw1/ (https://stream.zeno.fm/yw8poig9iwtuv)
ምላሽ ይስጡ