መስከረም 21 ቀን 2018(መናኸሪያ ሬዲዮ)ቻይና በሁቤ ግዛት የሚገኘውን የውሃን-ያንግሲን አውራ ጎዳና በመገንባት ዘመናዊ መሠረተ ልማትን ከባህላዊ የግብርና ሥራዎች ጋር ማዋሃድ እንደሚቻል በተግባር አሳይታለች። ይህ የ126 ኪሎ ሜትር ርዝመት ያለው መንገድ ዘላቂነት ያለው የምህንድስና አስደናቂ ምሳሌ ተደርጎ እየተወሰደ ነው።
የውሃን-ያንግሲን አውራ ጎዳና ዋነኛ ልዩ ባህሪው ሙሉ በሙሉ ማለት ይቻላል በአምዶች ላይ የተገነባ (Elevated) መሆኑ ነው። መንገዱ ከሩዝ እርሻዎችና ከአሳ ማጥመጃ ኩሬዎች በላይ በከፍታ ላይ ያልፋል እንጂ መሬት አይነካም ተብሏል።
ይህ አሠራር በመንገዱ ስር ያሉትን ውድ የእርሻ መሬቶች እንዳይበላሹ ወይም እንዳይባክኑ ሙሉ በሙሉ ይከላከላል። ገበሬዎችና ዓሳ አርቢዎች ከመንገዱ በታች ሆነው የዕለት ተዕለት ሥራቸውን (ግብርናና አኳካልቸር) ሳይስተጓጎሉ እንዲቀጥሉ አስችሏል።
መንገዱ የ100 ኪሎ ሜትር በሰዓት ፍጥነት ያለው ትራፊክ በቀላሉ መደገፍ የሚችል ሆኖ የተነደፈ ሲሆን፣ የውሃንና ያንግሲን አካባቢዎችን የትራንስፖርት ትስስር በእጅጉ አሻሽሏል ነው የተባለው።
ከአየር ላይ ሲታይ፣ አውራ ጎዳናው በውሃና በእርሻ መሬቶች ላይ በተዘረጋ በሚያንጸባርቅ ምንጣፍ ላይ የሚንሳፈፍ (floating) መስሎ ይታያል። ይህ የምህንድስና ጥበብ የዘመናዊነትን ፍላጎት ከ አካባቢያዊ ጥበቃ እና ባህላዊ የአኗኗር ዘይቤ ጋር የሚያጣጥም መፍትሄ መሆኑን ባለሙያዎች ይናገራሉ።
የቴሌግራም ቻናላችን ይቀላቀሉ 👉 https://t.me/menaharia_fm
__
ሀሳብ እና’ሳ’ፍራለን 📞
👉011-639-28-52
👉011-639-37-63
(https://stream.zeno.fm/yw8poig9iwtuv)
የቀጥታ ስርጭት 🔊 👉 https://zeno.fm/radio/menahria-99-1-3pw1/ (https://stream.zeno.fm/yw8poig9iwtuv)
ምላሽ ይስጡ