መስከረም 20 ቀን 2018(መናኸሪያ ሬዲዮ) የእስራኤል ጠቅላይ ሚኒስትር ቤንያሚን ኔታንያሁ በኳታር ዋና ከተማ ዶሃ ላይ እስራኤል በሰነዘረችው የአየር ጥቃት የኳታር ዜጋ በመገደሉ ይቅርታ መጠየቃቸው ተዘግቧል። ይቅርታው የቀረበው በዋይት ሀውስ ከዩናይትድ ስቴትስ ፕሬዝደንት ዶናልድ ትራምፕ ጋር ባደረጉት ውይይት ወቅት ለኳታር ጠቅላይ ሚኒስትር ሼክ መሐመድ ቢን አብዱልራህማን ቢን ጃሲም አል ታኒ በስልክ ጥሪ አማካኝነት ነው።
የኔታንያሁ ይቅርታ የእስራኤል ኃይሎች የኳታርን ሉዓላዊነት በመጣስ በሃማስ አመራሮች ላይ ያነጣጠረ ጥቃት መፈጸማቸውን ተከትሎ የመጣ ሲሆን፣ በዚህ ጥቃት ሳቢያ የኳታር የጸጥታ ሠራተኛ መገደሉን የዋይት ኃውስ ባወጣው መግለጫ አመልክቷል።
ጠቅላይ ሚኒስትር ኔታንያሁ ለኳታር ጠቅላይ ሚኒስትር ጥልቅ ፀፀታቸውን ገልጸው፣ ጥቃቱ ዒላማ ያደረገው ሃማስን እንጂ ኳታርን እንዳልሆነ እና ለወደፊቱም የኳታርን ሉዓላዊነት ዳግም እንደማይጥሱ ቃል መግባታቸው ተገልጿል።
ይህ ይቅርታ ኳታር በእስራኤል እና በሃማስ መካከል ባለው የሰላም ድርድር አስታራቂነቷን እንድትቀጥል ቁልፍ እርምጃ እንደሆነ ታዛቢዎች ገልጸዋል።
የቴሌግራም ቻናላችን ይቀላቀሉ 👉 https://t.me/menaharia_fm
__
ሀሳብ እና’ሳ’ፍራለን 📞
👉011-639-28-52
👉011-639-37-63
(https://stream.zeno.fm/yw8poig9iwtuv)
የቀጥታ ስርጭት 🔊 👉 https://zeno.fm/radio/menahria-99-1-3pw1/ (https://stream.zeno.fm/yw8poig9iwtuv)
ምላሽ ይስጡ